በአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የሐይማኖት ጉዳዮችና የሰላም ዕሴት ግንባታ ዘርፍ የ6ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ውይይት አደረገ።
በአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የሐይማኖት ጉዳዮችና የሰላም ዕሴት ግንባታ ዘርፍ የ6ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ውይይት አደረገ።
ጥር 06/2018 ዓ.ም (አ.አ.ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)
****
በአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የሐይማኖት ጉዳዮችና የሰላም ዕሴት ግንባታ ዘርፍ ከማእከል እስከ ወረዳ የተወጣጡ አስተባባሪዎች፣ ቡድን መሪዎች፣ፈጻሚዎች ጋር የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወር ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ውይይት አደረገ።
ለውይይት መነሻ የሚሆን ሪፖርት የዘርፉ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በሆኑት በአቶ ሙሉቀን እንየው የቀረበ ሲሆን፣በገለጻቸውም የሪፖርቱ አፈጻጸም ውይይት ቁልፍ ስራዎች አፈጻጸም አንጻር ምን ታቅዶ ምን ተሰራ የሚለውን፣የሰላም ዕሴት በመገንባትና የብዙኃነት ጉዳዮች በመተግበር ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማሳደግ እና የሰላም ዕሴት ሊገነቡ የሚችሉ ስልጠናዎችና ግንዛቤዎች ማስጨበጫ ስልጠና ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ለታዋቂ ግለሰቦች በመስጠት የህዝብ ለህዝብ ትስስርን ለማጠናከር ልዩ ልዩ ዘዴዎችን በመለየት የአቅም ባህል እንዲዳብር እና ነዋሪዎችን የሰላም ባለቤት ማድረግ ተችሏል።
በብሔራዊ በጎ ፍቃድ የተከናወኑ ተግባራት በሃይማኖትና እምነት ተቋማት ተከታዮቻቸው መካከል የመከባበር አብሮነትና ሴኩላሪዝም ባህል እንዲከበር ህጋዊ አሰራሮች ላይ በመመርኮዝ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ በከተማ ደረጃ ቤተ ዕምነቶችን የማደራጀት ስራ መሰራቱ፣በክ/ከተሞች በጥንካሬና በድክመት የታዩ ጉዳዮች ላይም በሪፖርቱ ተነስተዋል።
አቶ ሙልቀን አክለውም የሰላም ስልጠና፣የንቅናቄና ኮንፈረንስ ተግባራዊ ማድረግ፣የሐይማኖት አባቶች በመቻቻልና ሴኩላሪዝም ግንዛቤ ማስጨበጥ፣በሰላም ግንባታ በተሰጡ ስልጠናዎች የዕሴትና የብዙኃነት ጉዳዮች ላይ የፋይዳ ዳሰሳዊ ጥናት ማድረግ እና ሀገር በቀል የሆኑ ለሰላም ዕሴት ግንባታ አስተዋጽኦ ያላቸው ዕሴቶች እንዲለዩ ስራ መስራት የሚል በቀጣይ ትኩረት የሚደረግባቸው ዋና ዋና ተግባራት እንደሆኑም በሪፖርቱ አብራርተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የሐይማኖት ጉዳዮችና የሰላም ዕሴት ግንባታ ዘርፍ ም/ል ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሐኑ ረታ በሪፖርት ግምገማው ላይ በመገኘት፣በዚህ ስድስት ወራት ላይ በጥንካሬ የታየውን አጠናክሮ ማስቀጠልና የታዩ ድክመቶችን በማረም፣በቀጣይ የብዙኃነት ስልጠና ላይ፣የሰላም ኮንፈረንስና ንቅናቄዎችን ማወያየት፣የሰላምና በግብረ ገብ፣ክበባትና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን አቅም መውሰድ፣የሀገር ጉባኤዎች ምስረታ በየብሎኩ ማጠናከር ሚዲያዎችን ማሳተፍ፣የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤዎች ድጋፍ ማድረግ የተለያዩ አደረጃጀቶች መረጃ ማጠናከር እና መልካም አሰተዳደር ሊፈቱ የሚችሉ ችግሮችን መፍታት እንዳለባቸው ተናግረዋል ።
በመድረኩ ላይ አቶ ብርሐኑ ረታ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የሐይማኖት ጉዳዮችና የሰላም ዕሴት ግንባታ ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊን ጨምሮ ከማእከል እስከ ወረዳ የሚገኙ የዘርፉ አስተባባሪዎች ቡድን መሪዎችና ፈፃሚዎች እና የሰላም ሰራዊት አባላት ተገኝተዋል።