የጥምቀት በዓል ስራዎች ማስፈጸሚያ እቅድ ላይ ው...

image description
- recent news   

የጥምቀት በዓል ስራዎች ማስፈጸሚያ እቅድ ላይ ውይይት ተካሄደ።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ለክ/ከተማና ለወረዳ አመራሮች እንዲሁም ዳይሬክቶሬቶች የጥምቀት በዓል ስራዎች ማስፈጸሚያ እቅድ ላይ ውይይት አደረገ።
      ***
ጥር 02/2018 ዓ.ም

ቢሮዉ በ2018 የጥምቀት በዓል ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መልኩ ኃይማኖታዊ ትዉፊቱን ጠብቆ ያለምንም የፀጥታ ችግር ተከብሮ እንዲጠናቀቅ በማለም የበዓሉን ማስፈጸሚያ እቅድ እስከወረዳ ከሚገኙ የተቋሙ ፅ/ቤት ኃላፊዎችና ዳይሬክቶሬቶች  ጋር የጋራ ዉይይት አካሄዷል።

ወይይቱን የመሩት ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ሲሆኑ ኃላፊዋ እንደገለፁት ቢሮዉ በበጀት አመቱ መጀመሪያ ጀምሮ በከተማ አስተዳደሩ የነበሩ ሀገር አቀፍና አለም አቀፍ ሁነቶችና ኮንፈረንሶች እንዲሁም ትላልቅ የአደባባይ በዓላት በሰላም እንዲጠናቀቁ ከመላዉ የጸጥታ መዋቅር ጋር በመቀናጀት ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን አንስተዋል፤ 

በቀጣይ የሚከበረው የጥምቀት  በዓል ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መልኩ ኃይማኖታዊ ትዉፊቱን ጠብቆ እንዲከበር ካሳለፍናቸው የፀጥታ ስራዎች ተሞክሮ በመዉሰድ እቅዱን ማሳካት እንደሚገባ ገልፀዋል፤ 

ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ አክለዉም ከባለፈዉ አመት ባማረ መልኩ የህዝብ ለህዝብ ትስስርን የሚፈጥር የጥምቀት በዓል እንደፋይዳዉ ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ጠንካራ ስምሪት በመውሰድና እስከ ወረዳ ያለውን አመራርና ባለሙያ ከፀጥታ ኃይሉ ጋር ያለውን ትስስርና ቅንጅት በማስተሳሰር 7/24 መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል፤ 

ህዝብን ከጎናችን በማሰለፍ ባለፉት ጊዜያት ያከናወናቸዉ ተግባራት የተሻለ ተሞክሮ ያገኘንበት በመሆኑ  ያንኑ ለማስቀጠል እና በከተማችን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰፋፉ ሰዉ ተኮር የልማት ስራዎችን የሠራንበት፣ የህዝቡን ተጠቃሚነት አጉልተን ያሳየንበት፣ ህብረተሰቡ ከመንግስት ጋር እጅ ለእጅ የተያያዘበት ልማቱ ለማህበራዊ ለኢኮኖሚያዊና ለፓለቲካዊ እንቅስቃሴያችን መነቃቃት በፈጠረበት ማግስት በዓሉ መከበሩ ልዩ እንደሚያደርገው ገልፀው፤ በአሉ በሰላም እንዲከበር የጸጥታ ስራውን ማጠናከር እንደሚገባ አንስተዋል።