በአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

በአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የፀጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ የ6ወራት እቅድ አፈፃፀም ገመገመ፤

በአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የፀጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ የ6ወራት እቅድ አፈፃፀም ገመገመ፤ 

        ጥር 01/2018 ዓ.ም /አ.አ.ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ/
                 **
በአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የፀጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ ከማእከል እስከ ወረዳ ከተወጣጡ ከዘርፉ አስተባባሪዎች፣ ቡድን መሪዎችና ፈጻሚዎች ጋር የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወር ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ገመገመ።

ለመነሻ የሚሆን ሪፖርት የዘርፉ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በሆኑት በአቶ ዳምጠው አያሌው የቀረበ ሲሆን፣ በገለጻቸውም በ2018 በጀት ዓመት በ6ወራት ውስጥ በዘርፉ የተሰሩ ስራዎችን በግልፅነት ለሚመለከታቸው አካል ለማቅረብ የተሰሩ ስራዎች ጥንካሬዎችን ለማስቀጠል ውስንነቶችን በመቅረፍ በቀጣይ ግማሽ ዓመት ለሚሰሩ ስራዎች አቅም እንዲሆን ታላሚ ያደረገ ነው ብለዋል።

የዚህ ሪፖርት ግምገማ አስፈላጊነት በዘርፉ በ6 ወራት የስራ አፈጻጸም በምን ደረጃ ላይ እንዳለ እና የተሰሩ ስራዎችን ጠንካራ ጎኖችን የማስቀጠል ውስንነቶችን በመቅረፍ በቀጣይ ወራት የተሻለ የስራ አፈጻጸም ለማስመዝገብና ከፀጥታ ተቋማት ጋር በቅኝጅት የተሰሩ ስራዎችን በጋራ በመገምገም የከተማዋን ፀጥታና ደህንነት እንዲረጋገጥ ለማድረግ እንደሆነም አብራርተዋል።

ዳይሬክተሩ አክለውም በህገወጥ ተግባራትና በወንጀሎች ላይ ሲሳተፉ በተገኙ አካላት ላይም እርምጃን አጠናክሮ በመውሰድ የወንጀል ምጣኔን መቀነስ እንደተቻለ በመግለፅ የስጋት ቦታዎች ላይና ተቋማት ላይ ድንገተኛና ቋሚ ፍተሻ በማድረግ እንዲሁም በአዋኪ ተግባራት ላይ የተጠናከረ እርምጃ እንዲወሰድ የማድረግ ስራ መሰራቱን በሪፖርቱ አብራርተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የፀጥታና ኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ል ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድር በሪፖርት ግምገማው ላይ በመገኘት፣ከተማዋ ሰላምና ደህንነቷ አስተማማኝ ዘላቂ የሆነና ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ መረጃና ጥቆማ እንዲሰጥ በማድረግ፣ለአጋዥ የፀጥታ ሀይሎች ክትትልና ድጋፍ በመስጠት የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ማድረግ፣በከተማዋ ላይ የሚካሄዱ ጉባኤዎች፣ስብሰባዎችና ኩነቶች ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቁ መከታተል፣ ጨለማን ተገን ተደርጎ የሚካሄዱ ወንጀሎችን ዝርፊያዎችና ንጥቂያዎችን ህብረተሰቡ በየአካባቢው መብራት በማስወጣት መቀነስ፣ ስጋት የሚበዛባቸው ቦታዎችን በመለየት ስምሪት በመስጠት የፀጥታ ስጋቶችን መቀነስ፣የቅጥር ኤጀንሲዎችን ጥብቅ ክትትል ማድረግ ባለፉት ወራት በስፋት መሠራታቸውን በማንሳት በቀጣይም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል፤

በቀጣይ የሚከናወኑ ተግባራት ላይም በኃላፊው የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫ ተሰጥቶ ሰፊ ውይይት ማድረግ ተችሏል።

በመድረኩ ላይ አቶ ተስፋዬ ደንድር የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የፀጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊን ጨምሮ ከማእከል እስከ ወረዳ የሚገኙ የዘርፉ አስተባባሪዎች ቡድን መሪዎችና ፈፃሚዎች ተገኝተዋል።