የስትራቴጂክ ማኔጅመንት የቢሮዉን የ6 ወራት ሪፖ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የስትራቴጂክ ማኔጅመንት የቢሮዉን የ6 ወራት ሪፖርት አፈፃፀም

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የስትራቴጂክ ማኔጅመንት የቢሮዉን የ6 ወራት ሪፖርት አፈፃፀምና በቀጣይ ሳምንታት የሚከበረውን የጥምቀት በዓል እቅድ ከደንብ ማስከበር ባለስልጣን አመራሮች ጋር በጋራ ገመገመ።

      *****
ታህሳስ 30/2018 ዓ.ም

ቢሮዉ የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት እቅድ አፈፃፀምና በጥር  ወር መጀመሪያ የሚከበረው የጥምቀት በዓል ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መልኩና  ኃይማኖታዊ ትዉፊቱን ጠብቆ ያለምንም የፀጥታ ችግር ተከብሮ እንዲጠናቀቅ በማለም የበዓሉን ማስፈጸሚያ እቅድ ከደንብ ማስከበር አመራሮች ጋር የጋራ በማድረግ ዉይይት አካሄዷል።

ወይይቱን የመሩት ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ሲሆኑ ኃላፊዋ እንደገለፁት ቢሮዉ በተያዘው በጀት አመት መግቢያ ላይ አገልግሎት ፈላጊውን መላው የከተማውን ማህበረሰብ በማወያየት ወደ ትግበራ በመግባቱ ባለፉት 6ወራት በሰላምና ጸጥታ ዙሪያ አመርቂ ውጤት ከማስመዝገብ በተጨማሪ ከተማዋ የቱሪስት መስህብ እንድትሆን የማድረግ ስራ መሰራቱን አንስተዋል።

በከተማ አስተዳደሩ የነበሩ ሀገር አቀፍና አለም አቀፍ ሁነቶችና ኮንፈረንሶች እንዲሁም ትላልቅ የአደባባይ በዓላት በሰላም እንዲጠናቀቁ ከመላዉ የጸጥታ መዋቅርና የከተማው ነዋሪ ጋር በመቀናጀት ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን ኃላፊዋ ገልፀዋል።

የቢሮ ስትራቴጂክ ማኔጅመንት የጥምቀት በአል ሰላማዊ ለማድረግ የተዘጋጀዉ እቅድ ከተወያየ በኋላ ባለፉት 6 ወራት የጸጥታው አጠባበቅን አስተማማኝ ለማድረግ የሰላም ሰራዊቶችንና የቅጥር ጥበቃን እንደ አዲስ በመመልመልና ስልጠና በመስጠት ነባሩን አቀናጅቶ በማሰማራት ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት እንዲሆን በየአካባቢው ህብረተሰብ አቀፍ ውይይት በማድረግ፤ በመልካም አስተዳደርና በጸጥታ አጠባበቅ ዙሪያ እንዲወያዩ፣ የወንጀል ምጣኔዎች፣ የጸጉረ ልውጥ የሽብር ሀይል ሴራን የማክሸፍና በየአካባቢው የነበሩ ለወጣቶች አልባሌ ቦታ እንዲዉሉ ሲያደርጉ የነበሩ የቤቲን እና አረቄ ቤቶችን የመቆጣጠርና  በየቦታው የሚስተዋሉ ወንጀል የሚፈጸምባቸውን ቦታዎች የመለየት፣ የመቀነስና የመከላከል ስራ በሰፊው ከመሰራቱም በተጨማሪም የመሬት ወረራና ግንባታ ቁጥጥር በማድረግ ስርአት በማስያዝ ወደ መስመር እንዲገቡ የማድረግ ስራ በ6ወር ውስጥ በሰፊው መሰራቱን አንስተዋል።

ኃላፊዋ አያይዘውም በቀጣይ የሚከበረው የጥምቀት ቱባ በዓል ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መልኩ ኃይማኖታዊ ትዉፊቱን ጠብቆ እንዲከበር ካሳለፍናቸው የፀጥታ ስራዎች ተሞክሮ በመዉሰድ እቅዱን ማሳካት እንደሚገባ ገልፀዋል።

ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ በበኩላቸው ህዝብን ከጎናችን በማሰለፍ ባለፉት ጊዜያት ያከናወናቸዉ ተግባራት የተሻለ ተሞክሮ ያገኘንበት በመሆኑ  ያንኑ ለማስቀጠል እና በከተማችን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰፋፉ ሰዉ ተኮር የልማት ስራዎችን የሠራንበት፣ የህዝቡን ተጠቃሚነት አጉልተን ያሳየንበት፣ ህብረተሰቡ ከመንግስት ጋር እጅ ለእጅ የተያያዘበት፣  ልማቱ ለማህበራዊ፣ ለኢኮኖሚያዊና ለፓለቲካዊ እንቅስቃሴያችን መነቃቃት በፈጠረበት ማግስት በዓሉ መከበሩ ልዩ እንደሚያደርገው ገልፀው፤ በአሉ በሰላም እንዲከበር የጸጥታ ስራውን ማጠናከር እንደሚገባ አንስተዋል።

የበዓል ማስፈጸሚያ እቅዱና የ6 ወር አፈፃፀም ሰነድ በአቶ ማስረሻ ሀብቴ አማካኝነት ቀርቦ በስትራቴጂክ ማኔጅመንት አባላት ሰፊ ውይይት የተደረገበት ሲሆን፤
የተቋሙ የ6 ወራት እቅድ አፈፃፀምና የጥምቀት በዓል ማስፈፀሚያ እቅዱ በቀጣይ ቀናት በተዋረድ ውይይት እንደሚደረግበትም ተገልፃል፡፡