ቢሮው የህግ ማስከበርና የመልካም አስተዳደር ክላስተር አካላት ጋር የስድስት ወራት ቅንጅታዊ ስራዎች ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ገመገመ።
ቢሮው የህግ ማስከበርና የመልካም አስተዳደር ክላስተር አካላት ጋር የስድስት ወራት ቅንጅታዊ ስራዎች ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ገመገመ።
ታህሳስ 24/2018ዓ.ም
*****
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የቅንጅታዊ ስራዎች ዕቅድ አፈጻጸም ገምግሟል።
በግምገማው ወቅትም የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ የቢሮው አማካሪ የሆኑት አቶ ጌታሁን አበራ ሲሆኑ በንግግራቸውም የዛሬው ሪፖርት ግምገማ ዋና ዓላማ ሁሉም መስርያ ቤቶች በህግ የተሰጣቸውን ስልጣን በመጠቀም ተቀናጅተው የዜጎች ፍትህና መብት መጠበቅ እና ህግ በማስከበር የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ነው ብለዋል።
ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማውን ያቀረቡት የቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ አለምፀሐይ ማሞ ሲሆኑ በገለጻቸውም ወቅት፣ዋና ዋና ተግባራት፣የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ዕቅድ አፈጻጸም፣ቅንጅትንና ትብብርን በማጠናከር ወንጀሎችን የደንብ መተላለፍ ህገ-ወጥ ድርጊቶችን በመከላከል ሕግ ማስከበር፣የህዝብ አገልግሎት አቅርቦት ላይ ታማኝነት ተጠያቂነትና ግልፅነትን በማሳደግ የሙስና መከላከል እና የመልካም አስተዳደር ስርዓትን ለማረጋገጥ መቻሉን በሪፖርቱ አቅርበዋል።
የምሽት ትራንስፖርት አገልግሎት በሚሰጥበት አከባቢ ላይ ፖሊስ እንዲመደብ በማድረግ ደህንነቱ የጠበቀ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት፣ሚዲያዎችና የማህበረሰብ መድረኮችን በመጠቀም ዜጎች ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ማድረግ፣ሕግ ተላልፎ የተገኙ ግለሰቦችና ተቋማት ላይ እርምጃ የመውሰድ ስራ መስራታቸውንም በሪፖርቱ አንስተዋል።
የተቋማት ቅንጅታዊ አሰራር አስፈላጊ ነው ያሉት አማካሪው አቶ ጌታሁን የህግና መልካም አስተዳደር ዋና ዋና አገልግሎቶች፣ተቋማት መካከል ቴክኒካዊ ትብብርና መግባባት እንዲፈጠር የሚያደርግ ውጤታማ እንዲሆን አዳዲስ አሰራሮችን በመለየት ተግባራዊ እንደሚያደርግና ግንዛቤ እንደሚፈጥርም በሰነዱ አብራርተዋል።
አማካሪው አክለውም በቀጣይ ሪፖርት ላይ የተገኙ ውጤቶች በጥልቀት መታየት እንዳለበት እና የቀጣይ የትኩረት ስራዎች አቅጣጫ በቴክኒክ ኮሚቴ አማካኝነት የመስክ ምልከታ እና የስድት ወር አፈጻጸም በተቋሙ ክላስተር አመራሮች በሰላምና ፀጥታ የበላይ አስተባባሪነት ይገመገማል የሚል ተቀምጧል።
በመጨረሻም በመድረኩ የተገኙ ተሳታፊዎች የተለያዩ አስተያየቶችና ጥያቄዎች አንስተው፣መድረኩን የመሩት የቢሮው አመራሮች ማብራርያና ምላሽ ሰጥተዋል።
በመድረኩም የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አማካሪ አቶ ጌታሁን አበራ፣ ከከተማ አስተዳደር ካሉ ተቋማት የተወጣጡ ኃላፊዎችና ተወካዮች ተገኝተዋል።