ስድስተኛ ዙር አዲስ ምልምል የሰላም ሰራዊት አባ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

ስድስተኛ ዙር አዲስ ምልምል የሰላም ሰራዊት አባላትን በንድፈ ሀሳብና ወታደራዊ መስክ ለማሰልጠን ማስጀመርያ መርሐ-ግብር

በከተማዋ ላይ የሚፈጠሩ ወንጀሎችን በመቀነስ ረገድ የሰላም ሰራዊቱ ድርሻ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ።
    
ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ 

             ታህሳስ 21/2018 ዓ.ም(ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)
                           ****
ሀላፊዋ ይህንን የተናገሩት ቢሮው ከግዜ ወደ ግዜ አቅሙን በማጎልበት የከተማውን ሰላም አስተማማኝ ለማድረግ አቅሙን አጠናክሮ እያስቀጠለ የሚገኝ ሲሆን በዛሬው ዕለትም ስድስተኛ ዙር አዲስ ምልምል የሰላም ሰራዊት አባላትን በንድፈ ሀሳብና ወታደራዊ መስክ ለማሰልጠን ማስጀመርያ መርሐ-ግብር ላይ ሲሆን፤

በኮልፌ ክ/ከተማ የስልጠና ማስጀመሪያ መድረክ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ እንዳሉት በንቃት በቀጣይ የከተማውን ጸጥታ ለማስጠበቅ የሰላም ዘብ ለመሆን እጩ የሰላም ሰራዊት አባላት ለመሆን በፈቃደኝነት ለማገልገል ስለምታደርጉት ሁሉ ከልብ ምስጋናዬን አቀርባለው በማለት

ከተማችን አዲስ አበባ የኢኮኖሚ የፖለቲካ ሴንተር ለኑሮ ምቹ በለውጥ ደረጃ ላይም ትገኛለች ያሉት ሀላፊዋ ከተማዋ ከደረሰችበትን ፈጣን የዕድገት ደረጃ ጋር ተያይዞ ጠንካራ የጸጥታ አካላት መገንባት ከለውጡ በሏላ ከተማውን የሚመጥን በጸጥታው አጠባበቅም ከፍተኛ እርብርብ እየተደረገም እንደሆና በማስታወስ ዘላቂ ሰላም የሰፈነባት ከተማ እንድትሆንም እየተሰራ እንደሆና እየተሰራ ያለውን ዘላቂነት ያለው ሰላም ለማስቀጠል የማህበረሰቡ በተከታታይ አመታት ተሳትፎውን በማስቀጠል ተተኪነት የሌለው ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ህብረተሰቡን በማሳተፍና የሰላም ባለቤት አድርጎ ቢሮው እየሰራ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ለውጥ መምጣቱን ጠቅሰዋል።

ሀላፊዋ አያይዘውም የሰላም ሰራዊቱ አደረጃጀትን ህገ ደንብ በማውጣት የጸጥታ ስራውን በማቀናጀት ያለመ ተግባር በማከናወን በከተማ ደረጃ ግንባር ቀደም ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ያለፍት የአደባባይ ብሔራዊና ህዝባዊ በዓላት ያለ አንዳች የጸጥታ መደፍረስ በሰላም እንዲከበር ከማድረግም በተጨማሪም አብሮነታችንን ለአለም ህዝብ ማሳየት የቻልንበት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ  ከግዜ ወደ ግዜ አደረጃጀቱን በሰው ሀይል በመተካትና አቅሙን እያሳደገ መምጣቱን ገልፀዋል

አዲስ የተመለመላችሁት እጩ የሰላም ሰራዊት አባላት በቀጣይም ስልጠናው በትኩረትና በትጋት በመሰልጠን በቀጣይ በከተማው ላይ የሚታየውን ወንጀሎችን የጸዳ በማድረግ ጸጉረ ልውጥ እንቅስቃሴዎችን ንጥቂያዎችን በመቀነስ በመከላከያ በመቆጣጠር የልማት እንቅስቃሴዎች የከተማውን አቅም በማጎልበት የቱሪስት መስህብ የማድረግ ጉዞውን በማስቀጠል የከተማው ሰላም  ዘላቂነት አለኝታ ነኝ ብላችሁ በማሰብ  በትጋት እንድትሰሩ አደራ እላለው ሲሉ ተደምጠዋል ።

የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቴዎድሮስ ወ/ሚካኤል በበኩላቸው ለሰልጣኞች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት  በማስተላለፍ በየ አመቱ አዳዲስ የሰላም ሰራዊት አባላት  በማሰልጠን 6ኛ ኮርስ ላይ ስለ መድረሱን አንስተዉ አዲስ ምልምል የሰላም ሰራዊት በስልጠናዉ ማካተቱ አሁን ያለዉን ሰላም በላቀ ሁኔታ ለማረጋገጥ ነዉ በማለት በክፍለ ከተማዉ ፍጹም ሰላም እንዲሰፍን የሚረዳ ስልጠና ስለሆነ ሰልጣኞቹ በትኩረት እንዲከታተሉ አሳስበዋል።

በስልጠናው ማስጀመሪያ መድረክ ላይ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ፣አቶ ቴዎድሮስ ወ/ሚካኤል የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ፣አቶ አሚ ሙሄ አሊ የክ/ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ፣አቶ ጌታሁን አበራ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አማካሪ የጸጥታ አካላትን ጨምሮ ሎሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና እጩ ሰልጣኞች ተገኝተዋል።

ስልጠናው ለተከታታይ አስር ቀናት በሁሉም ክ/ከተሞች በንድፈ ሀሳብና በወታደራዊ መስክ ቀጣይነት እንደሚኖረውና በስልጠናውም 22ሺ እጩ የሰላም ሰራዊት አባላት እንደሚሳተፉ ለማወቅ ተችሏል።