በአዲስ አበባ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪ የ2018...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

በአዲስ አበባ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪ የ2018 ዓ.ም የ1ኛ ግማሽ አመት ምዘና ቅድመ ድጋፍና ክትትል

በአዲስ አበባ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰዉ ሃብት ልማት ቢሮ የተዋቀረ የድጋፍና ክትትል ቡድን በ2018 በጀት አመት የመጀመሪያው ግማሽ አመት በሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የተከናወኑ ተግባራትን ምልከታ አደረገ።
            ****
    ታህሳስ 20/2018 ዓ.ም(አ.አ.ሰ.ፀ.አ.ቢሮ)

በአዲስ አበባ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰዉ ሃብት ልማት ቢሮ  አማካኝነት  የ2018  ዓ.ም  የ1ኛ ግማሽ አመት  ምዘና ቅድመ ድጋፍና ክትትል በአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ተካሄደ።

ይህ የ2ኛ ሩብ አመት ድጋፍና ክትትል ለተቋማት ከፍተኛ ፋይዳ ያለዉና ተጠያቂነትን፣አሳታፊነትን እና የህግ የበላይነትን ያማከለ እንደሆነ እና  የመልካም አሰተዳደር ሰርዓትን ለማስፈን የሚኖረው ድርሻ ከፍተኛ መሆኑ ይታወቃል።

የድጋፍና ክትትሉ  ዓላማ የሪፎርም ስራዎች ምን ደረጃ ላይ እንዳሉ ከማመላከት  በተጨማሪ ከስትራቴጂክ  ግብ ጋር መንዝሮ ዕቅድ በመቅረጽ እና ስኮርካርድ በማዘጋጀት ተግባራቶቻቸውን ወደ ውጤት የለወጡትን ተቋማት ሆነ ግለሰብ ያሉበትን ሁኔታ በተቀመጡ የእይታ ነጥቦች አማካኝነት ምልከታ ማድረግ ሲሆን በምዘና ወቅት ደግሞ የማበረታቻ እና የእውቅና ሽልማት መርሃግብር በማዘጋጀት  ማበረታቻ ማድረግ  በየአመቱ የሚቀጥል ተግባር በመሆኑ ተቋማት በቂ ቅድመ ዝግጅት ማድረግ እንዳለባቸውም ይታወቃል።

በዛሬዉ እለት በአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ተገኝቶ ድጋፍና ክትትል ያደረገዉ ቡድን በክትትሉ ቼክ ሊስት ላይ በመመስረት የተቋሙ አመራሮችና የየ ዘርፉ ዳይሬክተሮች በተገኙበት ቢሮዉ  በሚሰጠው አገልግሎት አኳያ ተቋሙ በሪፎርሙ ያለበትን ሁኔታ ምልከታ አድርገዋል።

በድጋፍ ክትትሉ ወቅትም ቢሮዉ የተሻለ የቴክኖሎጂ አተገባበር፣የሪፎርም ስራዎቾና አገልግሎቱን አዘምኖ የተገልጋዮችን እርካታ ከመጨመር አኳያ ዘርፈ ብዙ ስራ በመስራቱ ቀጣይነት እንዲኖረዉ መትጋት እንዳለበት ተገልጿል። 

ድጋፍና ክትትሉን ያስጀመሩት የቢሮው ጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ተሻለ አክሊሉ  እንደገለፁት ቢሮዉ የተሻለ አፈጻጸም እና የተገልጋይ እርካታ እንዲኖረዉ ከተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች እስከ ባለሙያዎች የቢሮዉን አገልግሎት ለማሳለጥ እየተጋ እንደሚገኝ የገለጹ ሲሆን፤የድጋፍና ክትትል ቡድኑ በምልከታዉ የማጠቃለያ ላይ መልካም ግኝቶችን አበረታተዉ መሻሻል ባሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ የቃል ግብረ-መልስ ሰጥተዋል።