በ6ኛው ዙር የሰላም ሰራዊት የንድፈሃሳብና ወታደራዊ ስልጠና 22ሺ በጎ ፍቃደኞች እንደሚሳተፉ ተገለፀ።
በ6ኛው ዙር የሰላም ሰራዊት የንድፈሃሳብና ወታደራዊ ስልጠና 22ሺ በጎ ፍቃደኞች እንደሚሳተፉ ተገለፀ።
ታህሳስ 20/2018 ዓ.ም (ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)
*****
በአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ 6ኛ ዙር የሰላም ሰራዊት የንድፈሃሳብና ወታደራዊ ስልጠና ሊሰጥ እንደሆነና በስልጠናውም 22ሺ በጎ ፍቃደኞች እንደሚሳተፉ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ፍሰሐ ጥበቡ ገልጸዋል።
በከተማችን ላይ የተለያዩ አደረጃጀቶችን በተለይም የሰላም ሰራዊት አባላት በመፍጠር እና በማደራጀት የከተማዋን ሰላም በማስጠበቅ ትላልቅ አለም አቀፍ ስብሰባዎችን ጉባኤዎችንና የአደባባይ በዓላትን ያለምንም የፀጥት ችግር የሚካሄዱባትና የሚከበሩባት ከተማ ሆናለች።
በከተማችን ውስጥ የሰላም ሰራዊት አባላት በማደራጀት ከፀጥታ መዋቅር ጋር በማቀናጀት የከተማዋን ዘላቂና ሰላሟ የተረጋገጠባት ከተማ ከማድረግ ባሻገር፣ከዕለት ዕለት ቁጥራቸውን በመጨመረ ዘመናዊና በቴክኖሎጂ የተደገፉ አባል እንዲሆኑ እየተሰራ እንደሆነም ገልጸዋል።
በነገው ዕለት በከተማችን የሚጀመረው የሰላም ሰራዊት አባላት ስልጠና፣በስነ ምግባር የታነጹ ወታደራዊና ሳይንሳዊ ስልጠናዎችን ወስደው የከተማቸውን፣የብሎካቸውንና የአከባቢያቸውን ሰላምና ደህንነቷን ለማስጠብቅ የሚረዳ ስልጠና እንደሆነም አቶ ፍሰሐ አብራርተዋል።
የከተማዋን ሰላም ለማወክ በየጊዜው የሚንቀሳቀሱ የፀረ ሽብር ሀይሎችን፣ይህ አባል በበቁርጠኝነት ለሊት ተቀን በመስራት እና እኩይ ተግባራቸውን በማክሰም ከተማችን የትኛውንም ጉባኤዎች የሚካሄድባትና ተመራጭ ከተማ ለማድረግ ተችሏል ብለዋል።