በአገልግሎት አሰጣጥን በሳይንሳዊ የምዝገባና የንጽጽር ሂደት አገልግሎት ስታንዳርድ መተግበር ላይ የታዩ ክፍተቶችን ለመሙላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።
በአገልግሎት አሰጣጥን በሳይንሳዊ የምዝገባና የንጽጽር ሂደት አገልግሎት ስታንዳርድ መተግበር ላይ የታዩ ክፍተቶችን ለመሙላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።
ታህሳስ 17/2018 (ሰ/ፀ/አስ/ቢሮ)
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የስታንዳርዳይዜሽን ዳይሬክቶሬት ለማዕከል ሰራተኞችና ለክ/ከተማ አስተባባሪዎችና ቡድን መሪዎች በአገልግሎት አሰጣጥን በሳይንሳዊ የምዝገባና የንጽጽር ሂደት አገልግሎት ስታንዳርድ አፈጻጸም መተግበር ላይ የታዩ ክፍተቶችን በተመለከተ ላይ ስልጠና ሰጠ።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የስታንዳርዳይዜሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ አለምፀሐይ ማሞ እንዳሉት የዚህ ስልጠና አስፈላጊነት ዕቅዱ ላይ ያለውን ክፍተት ለመሙላት እና ዕቅዱ ተናባቢ ሲሆን የተቋም አፈጻጸም ውጤታማ የሆነና አመራሮቹም ሆኑ ሰራተኞች ይሄንን ተረድቶ በተሰጠው ስልጠና መሠረት ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።
ስልጠናውን የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰው ሀብት ቢሮ የሰው ሀብት ክትትል ቡድን መሪ አቶ እንዳልክ እንዳይላሉ የሰጡ ሲሆን፣በገለጻቸው ወቅትም የአገልግሎት ስታንዳርድ ፅንሰ ሀሳብ፣የአገልግሎት ተግባራትና ዝርዝር ተግባራት ልዩነት፣የተገልጋይና የሰራተኞች እርካታ ማሳደግ ስታራቴጂክ ግቦችን የሚዳስስ በሰነዱ አብራርተዋል።
አሰልጣኙ አክለውም የዚህ ስልጠና ዋና ዓላማ በየተቋሙ ያሉ አደረጃጀቶች ከላይ እስከታች በሚዛናዊ ስራ አመራርና ምዘና ስርዓት የተጣሉ ግቦች በየደረጃው ለሚገኙ ፈጻሚ አካላት በተሟላ ማውረድ የሚቻልበትን ስርዓት በማርጋት ለአፈጻጸም ክትትልና ግምገማ ምዘና ስራ ሁኔታ ለመፍጠር ነው።
አገልግሎት አሰጣጥ እንዲሻሻል የእያንዳንዱ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ኃላፊነት፣በዕውቀቶ በአመለካከት እና በክህሎት የተለወጠ፣ውጤታማ የሆነ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ማበራከትና የህብረተሰቡን እርካታ ማረጋገጥ አስፈላጊ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰው ሀብት ቢሮ የአገልግሎት ስታንዳርዴይዜሽን እና የአፈጻጸም ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ይመር ገልጸዋል።
አክለው ወ/ሮ ሰላማዊት ይመር በከተማ አስተዳደሩ ባሉ የመንግስት ተቋማት ውስጥ የሚሰጡ አገልግሎቶች እና ተቋማትን ስታንዳርዳይዝ በማድረግ የህብረተሰቡን አዳጊ ፍላጎት በሟሟላት የደንበኛውን እርካታ ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።
በመጨረሻም የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አማካሪ የሆኑ አቶ ጌታሁን አበራ የህዝቦች ደህንነትና ህግ ለማስከበር እንዲረጋገጥ የሚሰራ ተቋም እንደመሆኑ መጠን፣የዛሬው ስልጠና በፊት ከነበረን ዕውቀት የተሻለና አቅማችንን እንድናጎለብት የሚረዳ እንደሆነ ጠቅሰው፣አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚስተዋሉ ቅሬታዎችና እንግልቶችን መፍታትና መቅረፍ እንደሚገባም በማጠቃላይ አሳስበዋል።