ለስድስተኛ ዙር አዲስ ምልምል የሰላም ሰራዊት አባላት ስልጠና ለሚሰጡ የጸጥታ አካላት ኦረንቴሽን ተሰጠ።
ለስድስተኛ ዙር አዲስ ምልምል የሰላም ሰራዊት አባላት ስልጠና ለሚሰጡ የጸጥታ አካላት ኦረንቴሽን ተሰጠ።
ታህሳስ 16/2018 ዓ.ም(ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)
****
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የከተማውን ሰላም አስተማማኝ ለማድረግ ከጊዜ ወደ ጊዜ አቅሙን አጠናክሮ እያስቀጠለ የሚገኝ ሲሆን በቀጣይ ሳምንት በከተማ ደረጃ ተመልምለው ለስድስተኛ ጊዜ ወደ ሰላም ሰራዊት አባላት ለሚቀላቀሉ አካላት በንድፈ ሀሳብና ወታደራዊ መስክ ስልጠና ስልጠናውን በተግባር ለሚሰጡ የጸጥታ አካላት ኦረንቴሽን ተሰጥቷል።
በኦረንቴሽኑ ላይ በመገኝት መልዕክት ያስተላለፋት ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ እንዳሉት በከተማው ላይ ላለፉት በርካታ አመታት ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት አድርጎ በመስራት የአመለካከት የስምሪት ሌሎችንም ስልጠናዎችን በመስጠት አደረጃጀቶችንም በመፍጠር ለጸጥታው አጋዥ በመሆን አመርቂ ውጤት መመዝገቡን አንስተዋል፤
ለተመዘገበው ውጤትም መላው የከተማው ነዋሪ ሚናው ሰፊ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የጠላት ሀይል እንቅስቃሴዎች ታቅደው የነበሩ ወንጀሎችን በቁጥጥር ስር በማዋልና በመቀነስ የአደረጃጀት መዋቅሩንም በማዳበር ግልጽ በሆነ መንገድ ዘላቂ በሆነ መልኩ የከተማውን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ እንደተቻለም ገልጸዋል።
ሀላፊዋ አያይዘውም የሰላም ሰራዊቱ ተቋማዊ አደረጃጀቱን ጠብቆ በማቆየት ጥራት ያላቸው እንዲሆኑ የከተማው ሰላም አሌንታ ሆነው እንዲሰሩ ስምሪት በመስጠት የጸጥታው ስራ ያለ ምንም መደፍረስ አስተማማኝ በማድረግ ደረጃ በበጎ ፍቃደኝነት የሚጠናከር አደረጃጀት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል በማድረግ ከተማዋ እየገሰገሰችበት ካለው የእድገት ጎዳና አንጻር ተቋሙ ላይ የሚሰማራው አካል የወጣቶችን ተሳትፎ የሚያጎላ አካባቢውን የሚጠብቅ ማህበረሰብ ማፍራትም ተገቢ መሆን እንዳለበት በመጠቆም አዲስ የሚመለመለውና ወደ ሰራዊቱ የሚቀላቀለው የሰላም ሰራዊት አባላት ከጸጥታው አካል ጋር ተግባብቶ የሚሰራና በተደራጀ መልኩ መረጃን የሚሰጥ ቴክኖሎጂን የሚጠቀም አካባቢውን ከጸጉረ ልውጥ የሚጠብቅ ሰላምን ለሚያረጋግጠው ህብረተሰብ የሰላም ደሴት መፍጠር የተቻለው ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት ስላደረግን ነው ሲሉም አንስተዋል፤
ለአዲስ የሰላም ሰራዊት ምልምል የሰላም ሰራዊት አካላት የሚሰጠው ስልጠናም በፍጹም ዲሲፕሊን የሚመራ የሀገር ፍቅር ስሜት እንዲኖራቸው ለተልዕኮ በዘላቂነት የሚወጣ ሰራዊት በማፍራት የጸጥታው አካላት በተገቢው መንገድ ሀላፊነታችሁን እንድትወጡ አደራ እላለው በማለት አጽንኦት ሰተው ተናግረዋል ።
ስልጠናውን ለሚሰጡት የጸጥታ አካላት የማስፈጸሚያ ዕቅዱን ያቀረቡት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ም/ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ ፍስሐ ጥበብ ሲሆን ስለ ስልጠናው ነባራዊ ሁኔታ በተገቢው መንገድ ተግባራዊ መደረግ እንዳለበት ከገለጹ በኃላ ከጸጥታ አካላቱ ኦረንቴሽኑን መሰረት አድርገው ለሰጡት ሀሳብና አስተያየት ምላሽ ተሰጥቶበት መድረኩ ተጠናቋል።