በብልሹ አሰራር፣በስነ-ምግባር ምንነትና ሙስናን መታገል ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ።
ብልሹ አሰራርና ሙስናን መታገል ለተቋም ግንባታ ጎልህ ሚና እንዳለው ተገለፀ።
***
ታህሳስ 15/2018 (ሰ/ፀ/አስ/ቢሮ)
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ለማእከል ሰራተኞች፣ለክ/ከተማ አስተባባሪዎችና ቡድን መሪዎች በብልሹ አሰራር፣በስነ-ምግባር ምንነትና ሙስናን መታገል ዙሪያ ስልጠና ሰጠ።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰላም አምሳሉ እንዳሉት የዚህ ስልጠና ዋና ዓላማ ሙስናንና ብልሹ አሰራር ላይ በከተማውና በክ/ከተማ ያሉ ሰራተኞች በየጊዜው አቅማቸውን በማሳደግ የሙስናን መከላከል ትግሉን ማጠናከር ነው ብለዋል።
ስልጠናውም ሙስናን ከመከላከልና ከማስጠበቅ አኳያ በስራ ላይ ስነ-ምግባር፣ምንነት የስነ ምግባር ጉድለት የሚያስከትላቸው ጉዳቶች፣የሙያ ስነ-ምግባር፣መሠረታዊ መርሆዎችን የሚዳስስ ሰነድ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮምሽን ከፍተኛ የስልጠና ባለሙያ የሆኑት አቶ ደረጄ ግርማ አብራርተዋል።
በስልጠናውም የማእከል ሰራተኞች የክ/ከተማ አስተባባሪዎችና ቡድን መሪዎች ተሳትፈዋል።
በመጨረሻም ከተሳታፊዎች የተነሱ አስተያየቶችና ጥያቄዎችን ሰፊ የሆነ ውይይት ተደርጎበታል።