ኑ_እናገልግሎ
#ኑ_እናገልግሎ
በከተማችን የአገልግሎት አሰጣጡን አንድ እርምጃ ወደፊት ያራመደው የባለጉዳይ ቀን አገልግሎት አሰጣጥ በአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ በአንድ ማእከል እየተተገበረ ያለበት ሁኔታ...
***
ታህሳስ 15/2018 ዓ.ም (አ.አ.ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከማእከል እስከ ወረዳ ባሉ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አገልግሎቱን ለማሳለጥ ብሎም የተገልጋዩን እንግልት ለመቀነስ ታልሞ በባለጉዳይ ቀናት በዋናነት እሮብ እና አርብ ሙሉ ቀን በመጠቀም ግልፀኝነትን በሰፈነበት መልኩ አገልግሎት መሠጠት ከጀመረ ሰነባብቷል።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ዛሬ እለተ እሮብ መሆኑን አስመልክቶ ወደ ተቋሙ ጉዳይ ኖሯቸዉ የተገኙ ባለጉዳዮችን በአንድ ማእከል ኑ-እናገልግሎ የሚል መርህን በመከተል የባለጉዳዮችን ቅሬታና አቤቱታ በመፍታት አገልግሎት መስጠት ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ የባለጉዳይ ቀናትን ያስተገበረዉ በመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ግልፀኝነትን ለማስፈን፣ብልሹ አሰራርን ለማስቀረት እና ፈጣን ምላሽ መስጠትን ታሳቢ አድርጎ የተዘረጋ በመሆኑ የቢሮዉ አንድ ማእከል አገልግሎት አሰጣጥም ቀጣይነት የሚኖረዉ ስለመሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ከፍተኛ አመራሮች አንድ ማእከሉን በመሩበት ወቅት ገልጸዋል።