ቢሮው በመልካም አስተዳደር ዙሪያ ከአጠቃላይ ሰራ...

image description
- recent news   

ቢሮው በመልካም አስተዳደር ዙሪያ ከአጠቃላይ ሰራተኞች ጋር ውይይት አካሄደ።

ቢሮው በመልካም አስተዳደር ዙሪያ ከአጠቃላይ ሰራተኞች ጋር ውይይት አካሄደ።
       
             ታህሳስ 14/2018 ዓ.ም(ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)
                           ****
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ በከተማው ውስጥ ለሚገኙ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ መንግስታዊ ለሆኑም ላልሆኑም ተቋማት እንዲሁም ድርጅቶች የተለያዩ አገልግሎቶችን እንደሚሰጥ የሚታወቅ ሲሆን በቀጣይም ቀልጣፋና ተደራሽ አገልግሎትን ለመስጠት የሚያስችልና  መልካም አስተዳደር ላይ ያተኮረ ውይይት ከቢሮው ሰራተኞች ጋር አካሂዷል።

ውይይቱን የመሩት አቶ ጌታሁን አበራ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ አማካሪ መድረኩን በመሩበት ወቅት እንዳሉት ቢሮው  ከተሰጠው ስልጣናና ተግባር ጎን ለጎን በከተማ ላይ እጅግ በርካታ ስራን ከመስራት ጋር ተያይዞ የሰላም የደህንነት ህግ የማስከበር ስራን በመስራት በከተማው ላይ ዘላቂ ሰላምን ማምጣት መቻሉን ገልፀዋል፤

ቢሮው በከተማው ላይ ስራዎችን በበላይነት በማስተባበር በመስራት  ከአዲስ አበባ አልፎ ከሸገር ሲቲ ጋር በጋራ እየሰራና ውጤት እንዳስመዘገበም ጭምር አስታውሰው በቢሮው ውስጥ የሚሰሩ  የለውጥ ስራዎችም  አቅም እንዳላቸው ሰራተኞች በደንብ በመረዳት ስራን በተገቢው መንገድ በማከናወን የውስጥ ተነሳሽነትና ዝግጁነት ከሚባለው በላይ አስፈላጊ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ አስተሳስሮ በአዲስ እይታ ስራን በመተካት መስራት እንደሚያስፈልግ በመናገር ሰራተኞች በብዙ ነገሮች እራሳቸውን መለወጥ አለብኝ ብለው በማሰብ አዳዲስ ተሳትፎ በማድረግ ልምድ በመውሰድ በስልጠና የሚገኘውን በዕውቀትና በትብብር በመስራት የቢሮውን የለውጥ የመልካም አስተዳደር ስራዎች በቀጣይ በተቀላጠፈ መንገድ በመስራት የውስጥንም የውጭንም መልካም አስተዳደሮችን  በተገቢ መንገድ መፈጸም ይገባል ሲሉ ሀሳባቸውን ገልፀዋል ።