የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ በትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ያሉ ችግሮችና የአሰራር ስርዓት ላይ በጋራ በመሆን ገመገመ።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ በትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ያሉ ችግሮችና የአሰራር ስርዓት ላይ በጋራ በመሆን ገመገመ።
***
ታህሳስ 14/2018 (ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)
በግምገማው ላይ የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጡን በተመለከተ የሚዳስስ ዳሰሳዊ ጥናት ግኝት ውስጥ፣ኢንተርፕራይዞች ወይም አባላት በስራ ገበታቸው ላይ መገኘታቸውን እና አለመገኘታቸውን ማረጋገጥ፣የትራንስፖርት እጥረቶች የሚታይባቸውን ተርሚናሎች መለየት፣ቅንጅታዊ አሰራሮች ላይ ያሉትን ክፍተቶች፣ገንዘብ በሲስተም ማስተላለፍ ላይ የሚገጥሙ ችግሮችን መለየትና ሌሎች በዳሰሳ ጥናት የተገኙ ግኝቶች በሰነድ ቀርቦ ውይይት ተካሄዶበታል።
በግምገማው ወቅት፣ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ እንደተናገሩት በዋናነት እነዚህ አደረጃጀቶች ከህገ-ወጥ ብልሹ አሰራሮች ውጭ ሆነው እንዲሰሩ ድጋፍና ክትትል በማድረግ፣ህገ ወጥ ተሽከርካሪዎች ላይ የተወሰዱ እርምጃዎች በተለይም በባጃጅ ተሽከርካሪዎች ላይ የተወሰደ እርምጃ በከተማችን ላይ የሚስተዋሉ የሿሿ እና የተለያዩ በባጃጅ የሚከሰቱ ወንጀሎችን የቀረፉበት ሁኔታ እንዳለና ስርዓት የማስያዝ ስራዎች መሰራታቸውን አውስተው፣በከተማችን ውስጥ የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥና ስምሪት ላይ አሁንም ትኩረት ተሰጥቶበት ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
አቶ ዳኛቸው ሽፈራው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ በዳሰሳዊ ጥናት ግኝት ባቀረቡበት ወቅት እንዳሉት በተገኘው ዳሰሳዊ ጥናት ግምገማ ዋና ዓላማ የተመዘገቡ ውጤቶችን ማስቀጠልና ውስንነቶችን ለይቶ ማረም እንደሆነም ገልጸዋል።
በዳሰሳዊ ጥናት ግኝት ሪፖርት ላይም የተርሚናል አገልግሎት ክፍያን ሙሉ በሙሉ ከእጅ ንኪኪ በፀዳ መልኩ በሲስተም የሚያስከፍሉ ኢንተርፕራይዞችና የሚከፍሉ አገልግሎት ሰጪዎች መኖራቸው፣በአንዳንድ ተርሚናሎች የተርሚናል አገልግሎቱን በውል የወሰደው ኢንተርፕራይዝ የራሱን አባላት ብቻ ወደ ስራ ማሰማራት አገልግሎት እየሰጠ መሆኑና ህገ-ወጥ አሽከርካሪዎችን በተመለከተ በጥናቱ የታዩ በጠንካራ ጎኖችና የችግሩ ምንጭ እንደሆነም አብራርተዋል።
በመጨረሻም የቢሮው ሀላፊዋ በችግር ውስጥ ያሉትን የአደራጀናቸውን ኢንተርፕራይዞች ድጋፍና ክትትል በማድረግ ህግና ደንቡን ተደግፎ እንዲሰሩ ማድረግ፣የስነ ምግባር ችግር ያለባቸውን መስመር በማስያዝ መልሶ የማደራጀት የመደገፍ ስራ መስራት እና ከፀጥታ መዋቅሮች ጋራ ተቀናጅቶ መስራት እንዳለባቸው እንዲሁም በከተማው ላይ የሚሽከረከሩ የሞተር ሳይክል ከከተማ ውጭ የሆኑ ታርጋዎችን ክትትል በማድረግ የመለየትና ዳታ የመሰብሰብ ስራ ተሰርቶ ቀጣይ በመረጃዎች ተደግፎ በጋራ በመገምገም መስመር የማስያዝ ስራ እንደሚሰራ የቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።