በከተማችን ዘላቂና አስተማማኝ ሰላምን ለማስቀጠል ወጣቶች ጉልህ ሚና እንዳላቸው ተገለጸ።
በከተማችን ዘላቂና አስተማማኝ ሰላምን ለማስቀጠል ወጣቶች ጉልህ ሚና እንዳላቸው ተገለጸ።
*****
ታህሳስ 14/2018 (ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)
ስልጡን ወጣት፤ለከተማ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልፅግና!! በሚል መሪ ቃል ከከተማችን ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ጋር በመሆን በሰላም ዕሴት ግንባታ ዙሪያ ከከተማችን ወጣቶች ጋር ከብሎክ ጀምሮ እስከ ከተማ የውይይት መድረክ ጋር በተያያዘ ለሚመከታቸው አካላት ኦሬንቴሽን ተሰጠ፡፡
በመድረኩ ላይ የቢሮው ሃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እንዳነሱት እንደ ከተማችን የተለያዩ የሰላምና ጸጥታ ችግሮችን በወጣቶች ንቁ ተሳትፎ እንዲፈቱ ማድረግ ስለመቻሉ ገልጸው የዚህኛው መድረክ ዋና ዓላማን በተመለከተ ሲገልጹ ስልጡን ወጣት፤ለከተማ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልፅግና’’ በሚል መሪ ቃል ወጣቶች በከተማችን ሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ እንዲኖራቸው በማድረግ የአካባቢያቸውን ሰላምና ጸጥታ አስተማማኝ እንዲሆን ከህግ አስከባሪ አካላት ጋር ተቀናጅተው እንዲሰሩ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር ነው ብለዋል፡፡
ሀላፊዋ አያይዘውም የከተማችን ወጣቶች በሰላምና ሀገር ግንባታ ጉዳዮች ላይ የጠራ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማድረግ፤ በከተማዋና በመኖሪያ አካባቢያቸው ሰላምና ጸጥታን በማስከበር የሰላም ዘብነታቸውን አጠናክረው ማስቀጠል እንዲችሉ እና አሁን ያለውን የከተማችንን ፍጹም ሰላማዊነት በቀጣይነት ለማስቀጠል ወጣቶች እንደ ከዚህ ቀደሙ የነቃ ተሳትፎ ከማድረግ አኳያ ተግባራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ማስቻል ነው ብለዋል፡፡
አቶ በላይ ደጀን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርትና ወጣቶች ቢሮ ኃላፊ የወጣቶች ፖለቲካዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት በማስፋትና ባለቤት በማድረግ፣ጥያቄዎች ሲያነሱ በምክንያትና በንግግር በመወያየት የሚያምኑ ወጣቶችን በመፍጠር ለከተማው ሰላምና ደህንነት የበኩላቸውን ሚና መወጣት እንዳለባቸው ገልጸዋል።
የሁለቱም ቢሮ ቅንጅት ወሳኝ ነው ያሉት አቶ በላይ፣ወጣቶች ላይ የሚሰራው የግንዛቤ ማስጨበጫ እንዲሁም በየብሎኩና የመንደር ውይይትን በማስረጽ በቀጣይ የሚካሄደው ምርጫ በሰላማዊ መንገድ እንዲከናወን ይረዳል ብለዋል።
ለውይይቱ አስፈላጊ የሚሆኑ ቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናቀቅ፣በየወረዳው ከሚገኙ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት፣ለመድረኩ አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን ማሟላት እና የህዝብ ግንኙነት ስራዎችን አጠናክሮ መስራት የሚሉ ጉዳዮች በሰነድ ላይ ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
በመጨረሻም በውይይቱ የተሳተፉ ተሳታፊዎች አስተያየቶችንና ጥያቄዎችን አንስተዋል።