በትምህርት ቤቶች ውስጥ የሰላም ክበባት መቋቋም...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

በትምህርት ቤቶች ውስጥ የሰላም ክበባት መቋቋም በመልካም ስነ-ምግባር የታነጸ ትውልድ እንደሚፈጥር ተገለጸ።

በትምህርት ቤቶች ውስጥ የሰላም ክበባት መቋቋም በመልካም ስነ-ምግባር የታነጸ ትውልድ እንደሚፈጥር ተገለጸ። 
         
ታህሳስ 11/2018 ዓ.ም  (አ.አ.ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)
*****

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ እና የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ በጋራ በመሆን በሴኩላሪዝም አተገባበር እና በሰላም ግንባታ ትግበራ ላይ ከ11ዱም ክ/ከተሞች ለተወጣጡ ተማሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።

መድረኩን የከፈቱት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በንግግራቸው  በሴኩላሪዝም አተገባበር እና የሰላም ዕሴት ግንባታን በማጎልበት ተማሪዎች እርስ በርስ የመቻቻል በአብሮነት መኖር እንዴት ማዳበር እንዳለባቸውና መንግስት እያስቀጠላቸው ያሉ ተግባራት በትውልድ ቅቡቡሎሽ በመቀባባልና የትምህርት ስርዓቱን በማሻሻል ውጤት ሊመጣ እንደቻለና ከዚህ በፊት የነበሩ ተግዳሮቶች ሙሉ በሙሉ መቅረፍ እንደተቻለና በከተማችን ላይ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲፈጠር ሰፊ የሆነ ስራዎች መሰራቱን ተናግረዋል።

ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ አክለውም የዛሬው ስልጠና  በየትምህርት ቤቱ የሰላምን ክበባት እንዲቋቋም የተደረገበት አስፈላጊነት ተማሪዎች በዕውቀታቸው በአመለካከታቸው፣ግጭቶችንና ችግሮችን በንግግር እንዲፈቱ እና በመልካም ስነ-ምግባር ታንጸው እንዲያድጉ እንዲሁም ግጭቶች ከተፈጠሩ ቁጭ ብለው በውይይት የመፍታት፣የብዙኃነትና የአንድነት ባህልን፣በመቻቻል በአብሮነት የመኖር ልምድ እንዲሁም ሰላምን የማስረጽ፣ያዳበረና ያወቀ ዜጋን ለመፍጠር ነው ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ም/ል ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ረታ በመክፈቻ ንግግራቸው ላይ እንደተናገሩት የዛሬው ስልጠና ዋና ዓላማ ከከተማችን ትምህርት ቢሮ ጋራ በመሆን ያቀናጀነው ተማሪዎች በሰላም ዕሴት ግንባታ እና በሴኩላሪዝም አተገባበር በማስፋትና የማጎልበት ያላቸው ሚናና አውንታዊ የሰላም ዕሴት በተመለከተ የተማሪውን ሚና በተመለከተ ያለመ መድረክ ነው ብለዋል።

ሀላፊው አክለውም ከተማችን በአንድ በኩል ልማት በሌላ በኩል ሰላምን እያስጠበቀች ያለች ከተማ ስትሆን፣ቢሮው ሰላምን በተለይ ደግሞ በህብረተሰቡ ውስጥ በማስረጽና በማስፋት፣ግጭቶች ሲከሰቱ በማወያየት የሚፈታ ትውልድ እንዲዳብርና እንዲጎለብት የሚሰራና ጤናማ መስተጋብር እንዲኖር እንዲሁም የግጭት መንስሔዎችን በመለየት፣ግጭት ከተፈጠረም በውይይት እንዲፈታ የማድረግ ልምድ ማሳደግ ይገባል ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ም/ል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ ስልጠናውን የሰጡ ሲሆን በስልጠናቸውም፣ለሰላም ሰብዓዊ መብቶችና እስካውት ክበባት አስተባባሪዎች መምህራንና አባላት ተማሪዎች በትምህርት ተቋማት ከፀጥታና ሰላማዊ የመማር ማስተማር ጋር ተያይዞ ሰነድ አቅርበዋል።

በሰነዱም የሰላም ክበብ ዓላማ ተማሪዎች ዕውቀታቸውን አመለካከታቸውን በማዳበር የመተግበር፣የመቻቻል፣የመግባባትና የመከባበር ባህልና ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ የመፍታት ክህሎትን እንዲያጎለብቱ በማድረግ መልካም ስነ-ምግባር የተላበሰ ትውልድ እንዲኖር ማስቻል ነው ብለዋል።

አክለውም ሀላፊው የሰላም ክበብ ዋና ዋና ተግባራት፣በከተማ ደረጃ ሰላምን ከማስጠበቅ ጋር ተያይዞ ያላቸው ሚና እና የሰላም ክበብ በቅኝጅት ከሌሎች ክበባት ጋር የመስራት ሁኔታን በተመለከተ በሰነዱ አብራርተዋል።

በየትምህርት ቤቶች የተቋቋሙ የሰላም ክበባት አባላት ከት/ት ቤት ውጭ በየአከባቢያቸው የማፈጠሩ ግጭቶች የመከታተልና በስልጠናዎች ያገኛቿቸውን የሰላም ምንነት ግንዛቤ የመስጠትና የማስፋት ስራ መስራት በየት/ቤት ውስጥ የሰላም ክበባትን በማደራጀት፣ስልጠናዎች በመስጠት የማጎሎበት ሚናቸውን መወጣት እንዳለባቸው፣የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በማጠቃለያ ንግግራቸው አሳስበዋል።

#ዘገባው_የአዲስ_አበባ_ከተማ_ሰላምና_ፀጥታ_አስተዳደር ቢሮ_ነው

#በ8882 አጭር የነፃ ስልክ መስመራችን ማንኛውንም ጥቆማና መረጃዎች ያድርሱን ለተጨማሪ መረጃ ዌብሳይታችንን ይጎብኙ http://www.aaps.gov.et/