የቀጠለ ዘና
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ጋር በመቀናጀት ለግል የጥበቃ ኤጀንሲ አባላት፣ ለኮንዶሚኒየም መኖሪያ ቤትና ለማህበር ቤቶች ጥበቃዎች በወንጀል መከላከልና መቆጣጠር ዙሪያ 2ኛው ቀን የአቅም ግንባታ ስልጠና በ11ዱም ክ/ከተሞች በተደራጀ መልኩ እየተሰጠ ይገኛል፡፡
በቦሌ ክ/ከተማም የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድር፣ በፌደራል ፓሊስ የግል ጥበቃ ኤጀንሲ ቁጥጥርና ክትትል ሀላፊ ኮማንደር ሞላልኝ ወለላዉ፣ የቦሌ ክ/ከተማ ሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ መርዕድ አስፋውና 2ኛ ዙር ሰልጣኞች በተገኙበት ስልጠናው እየተሰጠ ይገኛል፡፡