የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ጋር በመቀናጀት በከተማዉ የሚከሰቱ ወንጀሎችን ለመቀነስ በማለም በወንጀል መከላከልና መቆጣጠር ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ።
የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ጋር በመቀናጀት በከተማዉ የሚከሰቱ ወንጀሎችን ለመቀነስ በማለም በወንጀል መከላከልና መቆጣጠር ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ።
****
ታህሳስ 10/2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የፀጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የወንጀልና የትራፊክ አደጋ መከላከል ም/ጠቅላይ መምሪያ ጋር በመቀናጀት ለግል የጥበቃ ኤጀንሲ አባላት፣ለጋራ መኖሪያ ቤትና ለማህበር ቤቶች ጥበቃዎች በወንጀል መከላከልና መቆጣጠር ዙሪያ የመጀመሪያ ዙር የአቅም ግንባታ የስልጠና በ11ዱም ክ/ከተሞች አካሂዷል።
በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የተካሄደዉ ስልጠና ላይ ተገኝተዉ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት አቶ ተስፋዬ ደንድር የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትል የቢሮ ሀላፊና የጸጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ ሀላፊ እንደገለፁት ስልጠናዉ ለ22,500 ለሚሆኑ ለግል የጥበቃ ኤጀንሲ አባላት፣ ለጋራ መኖሪያ ቤት ጥበቃዎችና ለማህበር ቤቶች ጥበቃዎች በወንጀል መከላከልና መቆጣጠር ዙሪያ በዛሬው እለት በ11ዱም ክፍለ ከተማ እየተሠጠ እንደሚገኝ በመግለፅ ከተማችን አዲስ አበባ ድሮ ከነበራት ገፅታ በእጅጉ እየተቀየረች ያለች በመሆኑ የጸጥታ አጠባበቅ ስራ ማጠናከር ያለብን ወሳኝ ወቅት ላይ እንዳለን አንስተዋል። ከዲጂታል አለሙ ጋር ተያይዞ በረቀቀ መንገድ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመቀነስ ወቅቱን ያገናዘበ የጸጥታ አጠባበቅ ስርዓት እንዲኖረን በየጊዜው የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ አስፈለጊ መሆኑን ተናግረዋል።
በመሆኑም የግልና የመንግስት ተቋማት ጥበቃዎች ሀላፊነታቸዉ በተሟላ ስነምግባር ሊወጣ እንደሚገባ አበክረዉ አንስተዋል።
የእለቱ የክብር እንግዳ አቶ ፍጹም ሀይሌ የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ በበኩላቸው ባለፍት 6 የለዉጥ አመታት በከተማ አስተዳደሩ ዘርፈ ብዙ ስራዎች እንዲሰሩ የጸጥታ መዋቅሩን በሪፎርም እንዲያልፍና ለግጭት መነሻ ሲሆኑ የነበሩ ጉዳዮችን እንዲስተካከሉ የፌደራልና የአዲስ አበባ ፓሊስ፣ የደንብ ማስከበር አባላትና የግልና የመንግስት ተቋማት የጥበቃ አባላትና መላ ህዝቡ ለነበራቸው አዎንታዊ ተሳትፎ አመስግነዋል።
የከተማዉን ሠላምና ጸጥታ አስተማማኝነት በማረጋገጥ ከተማዋ ከምታስተናግደዉ በርካታ ኩነቶች አንጻር የሰላምና ጸጥታን የማስከበር ስራችን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የግል የጥበቃ ኤጀንሲ አባላት፣የጋራ መኖሪያ ቤት ጥበቃዎችና የማህበር ቤቶች ጥበቃዎች ከዚህ በፊት ሀላፊነታቸውን ቢወጡም በአንዳንድ በግልና በመንግስት ተቋማት የጥበቃ አባላት ላይ የሚስተዋሉ የስነ ምግባርና የአመለካከት ግድፈቶች ከስልጠናዉ በመነሳት ማረም እንደሚገባ አበክረዉ አንስቷል።
የመክፈቻ ንግግሩ ተከትሎ በወንጀል መከላከልና መቆጣጠር ላይ ያተኮረ የስልጠና ሰነድ በኮማንደር ሀይሉ አስካለ የየካ ክፍለ ከተማ
ፓሊስ መምሪያ ምክትል አዛዥ አማካኝነት ቀርቦ በመንግስትም ሆነ በግል ተቋም የጥበቃ ስራ ስምሪት ወቅት ወንጀልን ከማስቀረት ረገድ መከናወን ባለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ዙሪያ ግንዛቤ ተፈጥሯል።
በመጨረሻም የቀረበዉን የስልጠና ሰነድ አስመልክቶና በጥበቃ ስራ ሂደት የሚገጥሙ ተግዳሮቶችን ዙሪያ ሰፊ ሀሳብና አስተያየት የተሠጠ ሲሆን ዉይይቱን የመሩት በኮማንደር ሀይሉ አስካለ የየካ ክፍለ ከተማ
ፓሊስ መምሪያ ምክትል አዛዥ፣ ኮማንደር አበበ አንበርብር የየካ ክፍለ ከተማ ማህበረሰብ አቀፍ ፓሊስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እና አቶ አለሙ ግርማ የየካ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት የፀጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ አስተባባሪ አማካኝነት ለተነሱት ጥያቄና አስተያየቶች ማብራሪያ በመስጠት ተጠናቋል።
ዛሬ ስራ ላይ የነበሩ የግልና የመንግስት የጥበቃ አባላት ደግሞ በነገዉ እለት የስልጠናው ተሳታፊ እንደሚሆኑ ይጠበቃል።