የማህበረሰቡን ደህንነት ለማስጠበቅ የሰላም ሰራዊት አባላትና የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ ቅንጅታዊ አሰራራቸውን አጠናክረው ማስቀጠል ይገባል ተባለ።
የማህበረሰቡን ደህንነት ለማስጠበቅ የሰላም ሰራዊት አባላትና የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ ቅንጅታዊ አሰራራቸውን አጠናክረው ማስቀጠል ይገባል ተባለ።
ታህሳስ 09/2018 ዓ.ም (አዲስ አበባ)
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከሰላም ሰራዊት አባላትና ከማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት አሰጣጥ ቅንጅታዊ አሰራርና ስምሪትን ለማጠናከር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።
በስልጠናውም ወቅት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ም/ል ቢሮ ኃላፊ አቶ ፍሰሐ ጥበቡ የእንኳን ደህና መጣቹና የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸውም ወቅት፣ከለውጡ በኃላ የከተማዋን ሰላም የተረጋገጠ እንዲሆን በህግ የተደገፈ የሰላም ሰራዊት አባላትን በማደራጀት ከፀጥታ አካላት ጋር በማቀናጀት እየተሰራ እንደሆነ አስታውሰው፣በከተማችን የሚስተናገዱ ትላልቅ ስብሰባዎች፣የአደባባይ በዓላቶች በሰላም እንዲጠናቀቁ፣በከተማችን የሚስታዋሉ ወንጀሎችን ለመቀንስ እንደተቻለና ማህበረሰቡ በሰላም እንዲቀሳቀሱና ሰላሟ የሰፈነባት ከተማ ለማድረግ ተችሏል ብለዋል።
ሀላፊው አክለውም የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ ሙያውን ጉልበቱን አስተዋጽኦ በማድረግ በማህበረሰብ ውስጥ የውስጥ ለውስጥ መብራት ማስበራት፣የአከባቢው ፀጥታ፣ፅዳትና አዋኪ ድርጊቶችን በመጠበቅ እንዲሁም የከተማችን ሰላም ሰራዊት አባላት ከፖሊስ ጋር በመቀናጀትና መረጃዎችን በመስጠት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ መወጣታቸውን ተናግረዋል።
አቶ ፍሰሐ አክለውም የዛሬው መድረክ ውይይት ዋና ዓላማ በቀጣይ የሚካሄደው ሀገራዊ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ የቅንጅት ስራዎቻችንን አጠናክሮ ለማስቀጠል እንድንወያይና ያገኘነውን ስኬቶችና ድሎች አንድናስቀጥል ነው ሲሉም ተደምጠዋል።
በውይይቱም የመወያያ ሰነድ የቀረበ ሲሆን፣ሰነዱንም ያቀረቡት፣የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ አቶ ውድነህ አቢ ሲሆኑ፣በገለጻቸው ወቅትም የዛሬ ውይይት የሰላም ሰራዊት አባላት በተሰጣቸው ደንብና መመሪያ መሰረት ከማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ ጋር በመቀናጀት የአከባቢያቸውን ፀጥታ በማስጠበቅ፣የህዝብ ተሳትፎ ምን እንደሚመስል፣ፖሊስ ከማህበረሰቡ ውጪ የሆነ ባህልና ዕሴቶችን በመቅረፍ ትውልዱንና ወጣቱን ወደመስመር እንዲገባ የማድረግ ስራ፣ወንጀል፣ግጭቶችን የደንብ መተላለፎችን እንዲሁም የማህበረሰብ ተኮር ውይይት አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትና የአከባቢያቸውን ሰላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ የመረጃ ቅብብሎሽንም የማደረጃት የማህበረሰብ አቀፍ ምክክር ማስቀጠል አንዳለባቸው በሰነዱ አብራርተዋል።
በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ ክ/ከተሞች በየወረዳዎቻቹ ያሉ የሰላም ሰራዊቶቻቹን ስምሪት ላይ የመንጠባጠብ ችግሮችን ለመቅረፍ የሰላም ሰራዊቶቻቹን በመወያየት ስምሪት መስጠት፣ነዋሪውን በጉልበት፣በሙያውና በገንዘቡ በማሳተፍ የሰላም ባለቤት ማድረግ፣በየብሎኩ የሚካሄዱ ማህበረሰብ አቀፍ ውይይቶችን የማጠናከር ስራዎችና እንዲሁም በዚህ ዓመት የሚካሄደው ሀገራዊ ምርጫ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲጠናቀቅና ህዝቡ በሰላማዊ መንገድ ምርጫውን እንዲሳተፉ ምቹ ሁኔታ መፍጠር እንዳለባቸው አቶ ፍሰሐ አሳስበዋል።
በውይይቱም ከአስራንዱም ክ/ከተሞች የተወጣጡ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ፣የሰላም ሰራዊት አባሎች እና የማዕከልና የክ/ከተሞች አስተባባሪዎችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
በጨረሻም ከተሳታፊዎች የተለያዩ አስተያየቶችና ጥያቄዎች አንስተው ከመድረኩ በቂ የሆነ ምላሽ ተሰጥቶበታል።
ዘገባው የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ነው
#በ8882 አጭር የነፃ ስልክ መስመራችን ማንኛውንም ጥቆማና መረጃዎች ያድርሱን ለተጨማሪ መረጃ ዌብሳይታችንን ይጎብኙ http://www.aaps.gov.et/