የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህግ ማስከበርና...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህግ ማስከበርና ቁጥጥር ንዑስ ኮሚቴ በህዳር ወር የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን ገመገመ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህግ ማስከበርና ቁጥጥር ንዑስ ኮሚቴ በህዳር ወር የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን ገመገመ።

ታህሳስ 8/2018 ዓ.ም (ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)

**

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ በከተማው ላይ ህገ-ወጥ የንግድ ስርዓት እንቅስቃሴን ለመቆጣጠር ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በጋራ እየሰራ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን በዛሬው ዕለትም በተቋሙ የሚመራው የህግ ማስከበርና ቁጥጥር ንዑስ ኮሚቴ በህዳር ወር የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን በመገምገም ቀጣይ የስራ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።

በህዳር ወር ዋና ዋና የህግ ማስከበር ቁጥጥር ንዑስ ኮሚቴው የሰራውን ስራ በተመለከተ ሪፖርት ያቀረቡት አቶ ተስፋዬ ደንድር የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊና የጸጥታና ኦፕሬሽን ዘርፍ ሀላፊ ገለፃ ሲያደርጉ እንዳሉት በከተማው ውስጥ በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ሲገበያዩና ምርት ሲደብቁ ሲያከማቹ ባልታደሰ ንግድ ፈቃድ ሲነግዱ የነበሩ ደረሰኝ የማይቆርጡና የኢኮኖሚ አሻጥር ሲፈጥሩ እንዲሁም የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴ በማድረግ በንግዱ እንቅስቃሴ ላይ እንቅፋት ሲፈጥሩ የነበሩ ህገ-ወጥ ነጋዴዎችና የገበያ ስርዓቱ እንዲስተጓጎል ያደረጉ ነጋዴዎች ላይ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ እርምጃ እንደተወሰደባቸው እየተወሰደባቸውም እንደሆነ ገልፀዋል።

ሀላፊው አያይዘውም ህገ-ወጥ ነጋዴዎችም ወደ ህጋዊነት እንዲመለሱ የማድረግ ስራን ከሸገር ከተማ አስተዳደር ጋር በጥምር በመሰራቱም በሁሉም አካባቢዎች ላይ የንግድ ቁጥጥር ስርአቱ ተጠናክሮ የማስኬድ ስራዎች መሰራታቸውንና በጥንካሬ በድክመት የተሰሩትን ስራዎች ሀላፊው በሚገባ አብራርተዋል።

መድረኩን የመሩት ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊና የግብረኃይሉ ሰብሳቤ ሲሆኑ በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እምርታ በሚል በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተቀመጡትን ግቦች ከማስተግበር አንፃር በኢንዱስትሪ በቱሪዝምና በከተማ ልማት ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ እንደሆነ ሀላፊዋ በማስታወስ

በከተማው ላይ የኑሮ ውድነትን በመቀነስ አቅርቦትን በማስፍት ማህበረሰቡ የሚፈልገውን አቅርቦት ተደራሽ በማድረግ ህብረተሰቡ በዋጋ ንረት ላይ የሚያነሳውን ቅሬታ መፍታትና የኢኮኖሚ አሻጥር የሚፈጥሩና ያለ አግባብ ዋጋ የሚጨምሩ ነጋዴዎች እንዳሉና ነዋሪውም የተቸገረበት ጉዳይ መሆኑ እየተስተዋለ መሆኑን አንስተው

ከአጎራባች ከተሞች ጋር በቅንጅት መሰራቱ ለውጥ በመምጣታቸው ላይ የተሰሩትን ስራዎች በማጠናከር አሁንም የቀሩና በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ላይ በርብርብ መስራት እንደሚጠበቅም ጭምር ሀሳባቸውን ገልጸዋል።

ሪፖርቱን መነሻ በማድረግ ከንዑስ ኮሚቴው አባላት ጋር ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን በተነሳው ሀሳብና አስተያየት ላይ በሀላፊዋ ምላሽ የተሠጠባቸዉ ሲሆን በቅንጅት ስራዉ ዉጤት ማስመዝገብ እንዲቻል የንግድ ስርዓቱ ላይ ህጋዊነትን ማስረጽ እንደሚገባ አመላክተዉ በሁሉም አቅጣጫዎች ዉጤት ለማስመዝገብ በቁጥጥሩ ስራ ዉጤታማ ስራ መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።

በመጨረሻም ክብርት ሀላፊዋ የቀጣይ አቅጣጫ ያስቀመጡ ሲሆን የኑሮ ዉድነቱን ለማርገብ ባልታደሰ የንግድ ፈቃድ የሚጠቀሙ አካላትን በአፋጣኝ እንዲያድሱ መስራት፣ የምርት አቅርቦትን መከታተል በቀረበዉ ላይ ደግሞ ህብረተሰቡ ጋር ያለዉን ተደራሽነት መከታተል፣ የግንዛቤ መፍጠር ስራ፣ከደላላ ነጻ የሆነ ግብይት መሆኑን ማረጋገጥ፣የገበያ ማእከላቶቹ ተመን ተለጥፎ እንደሚሸጥ መቆጣጠር፣ሁሉም የንግድ ተቋማት የዋጋ ዝርዝርማረጋገጥ፣የገበያ ማእከላቶቹ ተመን ተለጥፎ እንደሚሸጥ መቆጣጠር፣ሁሉም የንግድ ተቋማት የዋጋ ዝርዝር በአግባቡ መለጠፉን መቆጣጠር እና መሠል ተግባራትን በመከወን ህብረተሰቡ ፍትሃዊ የሆነ አገልግሎት እንዲያገኝ ለማድረግ ሁሉንም ምርት ባማከለ መልኩ አቅርቦቱ እንዲኖር የህግ ማስከበርና ቁጥጥር ንዑስ ኮሚቴው በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በመድረኩ ላይ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያን ጨምሮ የሰላምና ፀጥታ፤ የንግድ ቢሮ፤ የገቢዎች ቢሮ እና የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ም/ቢሮ ኃላፊዎችና የክ/ከተማና ወረዳ ፅ/ቤት ኃላፊዎች ተገኝተዋል፤

ዘገባው የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ነው

#በ8882 አጭር የነፃ ስልክ መስመራችን ማንኛውንም ጥቆማና መረጃዎች ያድርሱን ለተጨማሪ መረጃ ዌብሳይታችንን ይጎብኙ http://www.aaps.gov.et/