የመልካም አስተዳደር ችግሮች በጋራ ለመፍታት ከሀ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የመልካም አስተዳደር ችግሮች በጋራ ለመፍታት ከሀይማኖት አባቶች ጋር የተካሄደው ውይይት

ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደርና መንስኤዎች ሊሆኑ የሚችሉ ችግሮችን በመቅረፍ ሰላማዊ የሆነ አውድ መፍጠር እንደሚገባ ተገለጸ።

     ታህሳስ 07/2018 ዓ.ም (አዲስ አበባ)

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ስር ከሚገኙ አድባራት አስተዳደሪዎች ጋር የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በጋራ ለመፍታት የሚያስችል ውይይት አካሄደ።

በውይይቱም ለመወያያ የሚሆን ሰነድ የቀረበ ሲሆን፣ሰነዱንም ያቀረቡት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር የሰላም ዕሴትና የኃይማኖት ጉዳዮች ዘርፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን እንየው ሲሆኑ፣በገለጻቸው ወቅትም የዛሬ ውይይት ዋና ዓላማ፣ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመቅረፍና የሃይማኖት/እምነት መሪዎች ለሰላም መስፈን፣አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ነው ብለዋል።

አቶ ሙሉቀን አክለውም ሀገራችን ኢትዮጵያ በርካታ ሃይማኖታዊ ትውፊቶች ባለቤትና የረጅም ዓመታት ታሪክ ያላት ሀገር እንደመሆኗ መጠን፣ታታሪ ሕዝቦች ያላት፣ታሪካቸውን የሚያከብሩ፣ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲያሻግሩና የቀድሞ የአባቶቻቸውን ታሪካዊ ዳራና ትውፊት ጠብቀው ለትውልድ ማቀበል እንዳለባቸውም በሰነዱ አብራርተዋል።

የሃይማኖት ተቋማት ከተፈጥሮአዊ ባህሪያቸው በመነሳት ከሚያበረክቱት አስተዋጽኦ መካከል ለሃገር ግንባታ ለሰላም መስፈን፣በህዝቦች መካከልና መፈቃቀድ የሚሰሩ፣ለትውልድ ጥሩ ስነምግባር መታነጽ ለሀገርና ለሀገረ መንግስት መጽናት የብዙ ትውፊቶች ቅርሶችና የዕሴቶች ባለቤት እንደሆነም ገልጸዋል።

በሃይማኖት ተቋማት ያልተፈቱ ችግሮችና ምክክር የሚያስፈልጉ ጉዳዮችን ከሚመለከተው አካል ጋር በመወያየት እንደሚፈታ ጠቅሰው፣ቤተክርስቲያን ለሌሎች የፖለቲካ እና የጽንፈኛ ኃይሎች መጠቀሚያ እንዳይሆኑ አክብሮ መስራት እና የውስጥ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመደማመጥ፣በውይይት መፍታትና እንዲፈቱ ድጋፍ ማድረግ እንዳለባቸው ውይይቱን ያወያዩት አቶ ብርሃኑ ረታ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ም/ል ቢሮ ኃላፊ አሳስበዋል።

ሀላፊው አክለውም ቀጣይ የሚከበረው የጥምቀት በዓል የሚከበሩበት ቦታዎች በመወያየት ድጋፍ እንደሚደረግና እንዲሁም ካርታ የተሰጣቸው ቦታዎች እንዳሉና የተጠየቁትም ቦታ እየተሰራ እንደሆነ ገልጸዋል። 

በመጨረሻም ሁለተናዊ ብልፅግና ይሳካ ዘንድ ሁሉም በየድርሻው ያሉ አካላቶች ብዙኃነትን የአቀፈ ሀገር  እንድትሆን፣አባቶች በየአከባቢያቸው አብሮነትን፣መቻቻልን፣የጋራና የኃይማኖት ዕሴቶቻችንን ስርዓቱን ይዞ እንዲሻገር በተግባር ምሳሌ በመሆን እንዲሁም በውስጥ የሚፈጠሩ ግጭቶችና አለመግባባቶችን በመወያየትና በመነጋገር መፍታት እንዳለባቸው አቶ ብርሃኑ አሳስበዋል።

በአዲስ አበባ ውስጥ ከሚገኙ የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አድባራት የደብር አስተዳዳሪዎች፣ሰበካ ጉባኤ አባላት ፣ተሰብሳቢዎችና ቁጥጥር ሀላፊዎች በውይይቱ ተገኝተዋል።