ቢሮው ከማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎችና ቲክቶከሮች ጋር ውይይት አካሄደ።
ቢሮው ከማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎችና ቲክቶከሮች ጋር ውይይት አካሄደ።
ታህሳስ 3/2018 ዓ.ም (ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)
****
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የከተማውን ሰላም ለማረጋገጥ ህብረተሰቡ በሰላም ወጥቶ እንዲገባ ከተማው ላይ ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ በርካታ ስራዎች እየሰሩ እንደሚገኝ የሚታወቅ ሲሆን በዛሬው ዕለትም ከማህበራዊ ሚዲያ እንቂዎችና ቲክቶከሮች ጋር ውይይት አካሂዷል።
በውይይቱ ላይ በመገኝት እንኳን ደህና መጣችሁና መልዕክት ያስተላለፍት ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ እንዳሉት ጊዜው የድህረ እውነት ከመሆኑ ጋር ተያይዞና ሚዲያውም 4ኛው መንግስት እንደመሆኑ መጠን አጠቃቀማችን ምን ይመስላል በሚለዉ ላይ በእጅጉ አስፈላጊ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ አንድ ሀገር ስላለን አግባብነት ያለባቸው ጉዳዮች ላይ በመግባት አግባብነት የሌላቸው ጉዳዮች ላይ በጋራ መስራት ይጠበቅብናል በማለት
በሀሳብ ስንግባባ ለትውልድ ከማይጠቅም ሀሳብ ወጥተን በአዲስ አስተሳሰብ በመገስገስ የአሁኑ ትውልድ የሚመራትን ሀገር አንድ በማድረግ ያለውን አኩሪ ድል በሚመሰርት መልኩ የብልጽግና ፖርቲ እየሰራ እንደሚገኝም ክብርት ሊዲያ ገልፀዋል
አሁን ላይ ያለውን ዕድገት ወደ ተሻለ ማማ በማሻገር ትውልዱን ይዘን በጋራ ሀገሩን የሚወድ ከትውልድ ትውልድ የሚሻገር ቀሪ ስራ በማስቀመጥ ሀላፊነትን ከመወጣት ጎን ለጎን ሀገረ መንግስት ግንባታ ላይ በመስራት የኢትዮጵያን መጻኢ ዕድል ላይ በጋራ በመሳተፍ የነጠላ ትርክትን በመተው ኢትዩጵያዊነት ላይ የሚያምን ሁሉንም ብሔር በእኩል ሀሳብ የያዝ የኔነትን ስሜት ላይ ሳይሆን የእኛነት እሳቤን ይዞ የሚሰራ መንግስት እንዳለ ጠቁመዋል ።
ሀላፊዋ አያይዘውም ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ሰፊ ስራ እየተሰራና በጸጥታው ስራ ላይ እጅግ ለውጥ እንደመጣና በየአካባቢው የሚፈጠሩ የጸጥታ ችግሮችን ወዲያው እንዲፈቱ የማድረግ ስራ እየተሰራ እንደሆነና የሚዲያው አንቂዎች በቀጣይ ህግና ስርአትን አክብረውና ትውልዱ ላይ መስራት እንደሚገባና በቀጣይም በጋራ በቅንጅት አብረው እንደሚሰሩ ተናግረዋል ።
የሚዲያ አንቂዎቹ ሀሳባቸውን ሲገልጹ እንዳሉት ትውልዱ አስተሳሰብ ላይ የተሻለ ንቃተ ህሊና በመፍጠር ይዘው እንደሚሰሩ፣የሚዲያ አንቂው ማህበሩ የተሳሳተ አስተሳሰብ ላይ በተሻለ በቀጣይ ትኩረት ሰተው እንደሚሰሩና ሀገራዊና የዜግነት ግዴታቸውን እንደሚወጣ ተናግረዋል።
ለሚዲያ አንቂዎቹ የቢሮው ዋና ዋና ተልዕኮዎችን በዝርዝር ገለጻ ያቀረቡት አቶ ብርሀኑ ረታ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊና የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ ሲሆኑ በቀረው ገለፃ ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።