20ኛውን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀንን እና በሀገራችን ለ20ኛ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ34 ጊዜ እየተከበረ ያለውን የነጭ ሪቫን እና ጸረ ጾታዊ የጥቃት ቀንን አከበረ።
ቢሮው 20ኛውን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀንን እና በሀገራችን ለ20ኛ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ34 ጊዜ እየተከበረ ያለውን የነጭ ሪቫን እና ጸረ ጾታዊ የጥቃት ቀንን አከበረ።
ህዳር 29/2018 ዓ.ም(ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)
****
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ <<ዴሞክራሲ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት >> በሚል መሪ ቃል 20ኛውን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀንን እና በሀገራችን ለ20ኛ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ34 ጊዜ እየተከበረ ያለውን የነጭ ሪቫን እና ጸረ ጾታዊ የጥቃት ቀንን አከበረ።
በክብረ በዓሉ ላይ በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉት ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ እንዳሉት የሴቶችን ጥቃት በመቃወም እንደ መንግስት በከፍተኛ ደረጃ እየተሰራበት የሚገኝ ስራ እንደሆነ በመግለፅ ጥቃትን የማይቀበል ለትውልድ ግንባታ የሚተጋ በተለይ ደግሞ አሁን ላይ እየታየ ያለውን በርካታ ሴቶች ጥቃት እየደረሰባቸው ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የአመለካከትና የአረዳድ ደረጃ ስላለ አሁንም ሴቶች የኔ በሚሉት ሰው የጥቃቱ ሰለባ እየሆኑ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ከሚደርስባቸው ጥቃት ጋር ተያይዞም የስነ ልቦና ጫና እየደረሰባቸው ይገኛል ሲሉ ገልፀዋል።
እንደ ቢሮም ደግሞ ህግ አስከባሪ ከመሆናችን ጋር ተያይዞ ሀላፊነቱ በይበልጥ ሊገባን ጥቃቱም የደረሰባቸውን ሴቶች በማሰብ በቁርጠኝነት መስራት ይገባል ሲሉ ተደምጠዋል።
ሀላፊዋ አያይዘውም 20ኛውን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ኢትዮጵያ ሀገራችን ወደ ከፍታ የተጓዘችበት ህብረ ብሔራዊ አንድነታችንን ይዘን የቆየን ስንሆን በዛሬው ዕለትም በከፍተኛ ደረጃ እንደ ሀገረ እየተከበረ እንደሚገኝም ጭምር ጠቁመው ሀገራችን ህብረ ብሔራዊ አንድነት ያለባት ቀጣይነት ያለው የብልጽግና ጉዞ ይዘን ከኔነት ስሜት ወደ እኛነት በመቀልበስ ለሀገራችን በጋራ በመስራት ዲሞክራሲን የመገንባት ሀይልን ይዘን ለትውልድ ሊሻገር የሚችል አንድነቻችን ያማረ ሀገራችን ኢትዮጵያ በጋራ ክንዳችን እና በጽኑ እምነታችን ትስስራችን ለብዝሀነት ማዋል ይገባል ሲሉ ተደምጠዋል ።