የቅንጅታዊ ስራ የፊርማ ስነ-ስርዓት

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የቅንጅታዊ ስራ የፊርማ ስነ-ስርዓት

ቢሮው በህግ ማስከበርና በመልካም አስተዳደርና ስር ከሚመራው ዘርፈ ብዙ ቁልፍ ተቋማት ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችላቸውን የቅንጅታዊ ስራ የፊርማ ስነ-ስርዓት አካሄደ።

ህዳር 25/2018 ዓ.ም (ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)

****

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የከተማዋን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት የማድረግና የተቀላጠፈ የአግልግሎት አሰጣጥ አሰራሮችን አጠናክሮ ለማስቀጠል እንዲረዳ ቁልፍ ከሆኑ አስራ አራት ተቋማት ጋር በክላስተር አብሮ ለመስራት የሚያስችላቸውን የፊርማ ስነ ስርዓት አካሂዷል።

በጋራ ዕቅዱ ላይና የፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ በመገኝት ንግግር ያደረጉት ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ እንዳሉት ቅንጅታዊ ስራዎች መኖራቸው ለህብረተሰቡ የተሻለ ሁለንተናዊ ለውጥን ለማምጣት ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን የተሻለ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ በመገንባት በተናጠል ከመስራት ይልቅ በቅንጅት በመስራት ለውጡ ከፍተኛ ከመሆኑም በላም ከተማዋ በፈጣን የዕድገት ደረጃ ላይ እየገሰገሰች ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ቅንድታዊ ስራው አስፈላጊ እንደሆነ ሀላፊዋ በመግለፅ።

በተለይ የአገልግሎት አሰጣጥን አንድ በማድረግና በማዘመን ቀልጣፋ ፍትሀዊ በማድረግ በኩል የህብረተሰቡን ተሳትፎ ከማጎልበት ጎን ከጎን የህግ የበላይነትን ማስከበር አስፈላጊ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በህግ የመመራት ባህልን ማጽናት አፈጻጸምን በማጎልበት በጋራ ተግባቦትን በመፍጠር በተለይም ደግሞ ሌብነትና ብልሹ አሰራርን ለማስፈን ይረዳልም ሲሉ ክብርት ሀላፊው ተናግረዋል።

የጋራ ዕቅዱን መነሻ ጹሁፍ ያቀረቡት ወ/ሮ አለም ጸሀይ ማሞ የቢሮው የአግልግሎት ስታንዳርዳይዜሽን ዝግጅት ክትትልና ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሲሆኑ በክላስተር ውስጥ ካሉ ቁልፍ አስራ አራት ተቋማት ጋር የፊርማ ስነ-ስርዓቱ ተካሂዷል።