የቀጠለ ዜና
ትናንት የተጀመረው "ትውልድን በስነ-ምግባር ተቋምን በአሰራር " በሚል መሪ ቃል የሚከበረው ዓለም አቀፍ የጸረ ሙስና ቀን ዛሬ ተጠናቋል።
ህዳር 20/2018 ዓ.ም (ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)
****
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ዳይሬክቶሬት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ22ኛ ግዜ እየተከበረ የሚገኝውን የጸረ ሙስና ቀን ከማዕከል እስከ ወረዳ ድረስ ከሚገኙ አጠቃላይ ሰራተኞች ጋር ከትናንት ጀምሮ ስካሄድ የቆየ የንቅናቄና የስልጠና መድረክ ዛሬ ተጠናቋል።
መድረኩ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ጸረ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮምሽን የስልጠና ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ግዛቸው ማሩ ንግግር ያደረጉበት ወክት፤ ኮምሽኑ አሰራርን በማዘመን በትውልድ ግንባታ ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን እንድሁም ሙስናን የሚጸየፍ የወደፊት ትውልዱን በስነ ምግባር በማነጽ የተሻለ አስተሳሰብ በመፍጠር ላይ በርካታ ግንዛቤዎችን በመፍጠር ሰፊ ስራዎች እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው፤ ሙስናን በመከላከል ሂደት ውስጥ በሙስና የሚገኙ ንብረቶችን ወደ መንግስት ካዝና ማስመለስ መቻሉንና ተጠያቂ በማድረግ ዙሪያ በርካታ ስራዎች እንደተሰሩ ገልጸዋል።
አቶ ግዛቸው አክለውም መስና መጥፋት የሚቻለው ውስጣችን በጎ አስተሳሰብ ሲኖር በመሆኑ ትውልድን ለመገንባት መንግስት አሰራር ዘርግቶ በትምህርት ቤት የግብረገብ ትምህርት እንድሰጥ ማድረጉንና ግብረገብ የሰው ፀባይን እና ድርጊትን የሚአደናግግ መሆኑ ጠቅመዋል።
የስልጠናውን መነሻ ጽሁፍ ያቀረቡት አቶ አቤል ሳኩሜ ከስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮምሽን ከፍተኛ የስልጠና ባለሙያ ሲሆኑ ስለ ስልጠናው ዓላማ፣ስለ ስነ ምግባር፣ምንነት ምንጮቹ፣ስለ ህጉና ስለሙስና ተጋላጭነት ስለሚያስከትለው ጉዳት ሰፊ ማብራርያ በመስጠት ሙስና ለመከላከል አስተዳደራዊ አሰራር፣ ማህበራዊ ትስስር እና ጠንካራ የህግ ስርዓት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
መድረኩን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ዳይረክቶሬት ዳይረክተር አቶ ሰላም አምሳሉ፣ ሙስናን በተመለከተ በየትምህርት ቤት በመቋቋም እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው አንድ ቀን በተፈጸመው ሙስና የተፈጸመበት ሰው እድመ ልኩ ህይወቱ ልበላሽበት ይችላልና ውስጣችን ቁጭት ልኖር ይገባል በማለት የሰላም እና ፀጥታ ሰራተኞች የከተማችን ሰላም ለማረጋገጥ ከሌሎች የመንግስት ሰራተኞች በላይ ሙስና ለመከለል መታገል ይገባል ብለዋል።
በመድረኩ ላይም የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ዳይረክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰላም አምሳሉ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ስስነምግባርና ጸረ ሙስና ኮምሽን የስልጠና ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ግዛቸው ማሩ እና የአዲስ አበባ ከተማ ስስነምግባርና ጸረ ሙስና ኮምሽን ባለሙያ አቶ አቤል ሳኩሜ ጨምሮ ከማዕከል እስከ ወረዳ የሚገኙ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ዳይረክተሮች፣ አስተባባሪዎች፣ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች ተገኝተዎል።