ዓለም አቀፍ የጸረ ሙስና ቀን ተከበረ።
<ትውልድን በስነ-ምግባር ተቋምን በአሰራር >>
በሚል መሪ ቃል ዓለም አቀፍ የጸረ ሙስና ቀን ተከበረ።
ህዳር 19/2018 ዓ.ም (ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)
****
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የጸረ ምግባርና ጸረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ክፍል በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ22ኛ ግዜ እየተከበረ የሚገኝውን የጸረ ሙስና ቀን ከማዕከል እስከ ወረዳ ድረስ ከሚገኙ አጠቃላይ ሰራተኞች ጋር የንቅናቄና የስልጠና መድረክ አካሄዷል።
በመድረኩ ላይ በመገኝት መልዕክት ያስተላለፍት አቶ ግዛቸው ማሩ የአዲስ አበባ ጸረ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮምሽን የስልጠና ቡድን መሪ እንዳሉት የአዲስ አበባ ጸረ ሙስናና ስነ ምግባር ተቋም ተቋቁሞ ወደ ስራ ከገባ ጀምሮ ኮምሽኑ አሰራርን በማዘመን በትውልድ ግንባታ ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ይገኛል በማለት ሙስናን በመከላከልና በመቆጣጠር ብሎም የሚጸየፍ የወደፊት ትውልዱን በስነ ምግባር በማነጽ የተሻለ አስተሳሰብ በመፍጠር ላይ በርካታ ግንዛቤዎችን በመፍጠር በኩል የበኩሉን አስተዋጽኦ እየተወጣ እንደሆነ በመጠቆም
ሙስናን በመከላከል ሂደት ውስጥ የመንግስት ንብረትና ምዝበራን ለማቋም እንደተቻለና በሙስና የሚገኙ ንብረቶችን ወደ መንግስት ካዝና ከማስመለስ ጎን ለጎን ተጠያቂ እያደረገ እንደሚገኝና ውጤቱም ተጨባጭ እየሆነ እንደመጣ ገልጸዋል ።
የስልጠናውን መነሻ ጽሁፍ ያቀረቡት አቶ አቤል ሳኩሜ ከስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮምሽን ከፍተኛ የስልጠና ባለሙያ ሲሆኑ ስለ ስልጠናው ዓላማ፣ስለ ስነ ምግባር፣ምንነት ምንጮቹ፣ስለ ህጉና ስለሙስና ተጋላጭነት ስለሚያስከትለው ጉዳት በተመለከተ ሰፊ የስልጠና ሰነድ አቅርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።
የስልጠናው መነሻ ጽሀፍ መሰረት ተደርጎ ለተነሳው ሀሳብና አስተያየት ምላሽና ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን ስልጠናው በነገው ዕለትም ቀጥሎ እንደሚውል ለማወቅ ተችሏል።