የቀጠለ ዜና
በከተማው ውስጥ የሚገኙ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች ለጸጥታው ስራ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ ቀረበ ።
ህዳር 18/2018 ዓ.ም(ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)
****
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የጸጥታና ኦፕሬሽን ዘርፍ በከተማው ውስጥ ለሚገኙ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎችና አባላት በወንጀል መከላከልና መቆጣጠር ላይ ከትላንቱ የቀጠለ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።
በስልጠናው ላይ በመገኝች መልዕክት ያስተላፉት አቶ ተስፋዬ ደንድር የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊና የጸጥታና ኦፕሬሽን ዘርፍ ሀላፊ እንዳሉት አዲስ አበባ ከተማ በፈጣን የእድገት ግስጋሴና ለውጥ ላይ የምትገኝ ለውጧም ከግዜ ወደ ግዜ በፈጣን ኢደት ላይ ያለች ውጤቱም ተጨባጭና የሚታይ እንደመሆኑ መጠን በዚህ የለውጥ ኢደት ውስጥ ደግሞ የከተማው ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ መላው የከተማው ነዋሪ በጋራ ያመጣው ለውጥ መሆኑን የጠቀሱት ሀላፊው
የኮሪደር ልማቱ በተለይ ደግሞ የትራፊክ መጨናነቅንና የወንጀል ምጣኔን ከመቀነሱ ጎን ለጎን ንጹህ የሆነ የተፈጥሮ አየርን ከመተንፈስ ለመጭው ትውልድ ተስፋንና አላማን ይዞ የመጣ በከተማው አመራር በህብረተሰቡ ተሳትፎ ጋር ተያይዞ ሰላም የሁሉም መሰረት እንደመሆኑ መጠን ወንጀልን በመከላከልና በመቆጣጠር ላይ የሁሉም ማህበረሰብ ተሳትፎና ሀላፊነት እንደሚያስፈልግና በተለይም ደግሞ በሞተር ሳይክር ለህብረተሰቡ አገልግሎት በሚሰጥበት ግዜ በእንቅስቃሴዎች መሀል የሚታዩ የሚፈጠሩ ድርጊቶች ስለሚኖሩ በጋራ መከላከል እንደሚገባና በከተማው ላይ የታየውን አስተማማኝ ሰላም በቀጣይ ዘላቂ ለማድረግ በጋራ በመስራት አስፈላጊ እንደመሆኑ መጠን
ከጸጥታው ሀይሉና አጋዥ አካላት ጋር መላሙ የከተማው ማህበረሰብ ተሳትፊውን በማጠናከር አልፎ አልፎ የሚፈጠሩ የወንጀል ድርጊቶችንና የጸጉረ ለውጥ እንቅስቃሴዎች ላይ ትኩረት በማድረግ የስልጠናው ዓላማ በማሳካትና የከተማው ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥና ማህበረሰቡ በሰላም ወቶ እንዲገባ የበኩላችሁን አስተዋጽኦ እንድትወጡ አደራ እላለው ሲሉ ተደምጠዋል ።
መድረኩን የመሩት አቶ ተስፋዬ ደንድር የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊና የጸጥታና ኦፕሬሽን ዘርፍ ሀላፊ፣ኮማንደር ገዛኸኝ ጌታነህ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የወንጀል ና ትራፊክ አደጋ መከላከል ም/አዛዥ፣ኢንስቴክተር ሰለሞን አዳነ የትራፊክ ሞያና ህዝብ ግንዛቤ ዲቪዝዩን ሀላፊዎች ሲሆኑ ከሰልጣኞቹ ስልጠናውን መሰረት አድርጎ ለተነሳው ሀሳብና አስተያየት ምላሽና ማብራሪያ ሰተውበታል።
በወንጀል መከላከልና መቆጣጠር ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናውን የሰጡት ም/ኮማንደር ታዲዎስ አክሊሉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ማህበረሰብ አቀፍ ጥናትና ዕቅድ ትንተና ዲቪዚዩን ሀላፊ ሲሆኑ ከህግ አንድምታ፣ወንጀልን መከላከያ እርምጃዎ ቴክኖሎጂ በወንጀል ስለመከላከልና ምንነቶቹ ዙሪያ ገለፃ አድርገዋል።