የእንኳን ደህና መጣችሁ ፕሮግራም

image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የእንኳን ደህና መጣችሁ ፕሮግራም

ለ14ኛ ዙር ብሔራዊ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች የእንኳን ደህና መጣችሁ ፕሮግራም ተካሄደ ።

   ህዳር 16/2018 ዓ.ም(ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)
                           ****
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ከተለያዩ ክልሎች በበጎ ፈቃደኝነት ሰልጥነው ወደ አዲስ አበባ ከተማ በመምጣትና በጎ ተግባርን ተላብሰው በጎ ፈቃደኛ ለሆኑ ወጣቶች የእንኳን ደህና መጣችሁ መረሐ ግብር አካሂዷል።

በመርሐ ግብሩ ላይ በመገኝት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት አቶ ሙሉቀን እንየው የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እንዳሉት ውብ እና ድንቅ ከተማ ወደሆነችው አዲስ አበባ ከተማ እንኳን በደህና መጣችሁ ካሉ በሏላ የበጎ ስራ ተግባር የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀሳብ መሆኑን አስታውሰው ጅማሮው ተግባራዊ ከሆነ ግዜ አንስቶ ተግባር ላይ ውሎ ስኬትን ይዞ የተጓዘ እንደሆነና ቀጣይነትም ያለው እንደሚሆን በመግለፅ በበጎነት ተግባር ላይ ስትሳተፍ ችግሮች ቢገጥሙ እንኳን በውይይትና በንግግር በመፍታት አብሮነትን ማጠናከር እንደሚገባና አዲስ ህይወት ሲጀመር ሁሉም ነገር ምቾች ሊኖረው ስለማይችል ከህብረተሰቡ ጋር በመላመድ በመግባባት በሚኖረው በጎ ተግባር ላይ በመሳተፍ  በከተማው ላይ ብዙ ብሔሮችና ብሔረሰቦች ተቻችለው የሚኖሩባት ከተማ እንደመሆኗ መጠን በሚኖራችሁ ቆይታ ሁሉ መልካም ነገር እንዲገጥማችሁ እመኛለሁ ሲሉ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

አቶ እንዳለ ጸጋዩ የሀይማኖት ጉዳዮች ከፍተኛ ባለሙያ በመድረኩ በመገኝት እንዳሉት የሚገጥሙ ችግሮችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር በቀጣይ ግዜአት መፍትሔ እንደሚሰጠውና ለመጡበትና ላላሙበት ግብ ከዳር በመድረስ የበጎነት ተግባርን በተሰማራችሁበት  ልክ እንድትወጡ አደራ እላለው ሲሉ ሀሳባቸውን ገልጸዋል።

ወጣቶቹ ስለሚኖራቸው ቆይታና የበጎነትን ዓላማ ላይ  ገለፃ ያደረጉት አቶ ኤልያስ ቀጄላ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ የስልጠና  ቡድን መሪ ሲሆኑ 
ሀገርና ወገንን ለመደገፍ የሚደረገው ጥረት የሚበረታታና የመደገፉ እንደመሆኑ መጠን ክህሎትን በማዳበር ለሰዎች ድጋፍን በማድረግ ውስጥ ከገንዘብ በላይ የሚገኝው የህሊና እርካታ ለማግኝት ሰላምን በማግኘት ዜጋን ማገልገል የማይገኝ ዕድል እንደመሆኑ መጠን በተገቢው መንገድ እንዴት ተግባራዊ እንደሚያደርጉ አብራርተዋል ።

ወጣቶቹ አሁን ላይ ስላሉበት ሁኔታና በቀጣይ ስለሚኖራቸው ቆይታ መስተካከል ስለሚገባው ጉዳዩችን በተመለከት ሀሳብና አስተያየት የሰጡ ሲሆን ከመድረክ መሪዎቹ ምላሽ ተሰጥቶበታል።