ቢሮዉ በከተማዉ ለሚገኙ የሞተር ማህበር አመራሮችና አባላት በወንጀል መከላከልና መቆጣጠር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።
ቢሮዉ በከተማዉ ለሚገኙ የሞተር ማህበር አመራሮችና አባላት በወንጀል መከላከልና መቆጣጠር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።
*****
ህዳር 16/2018 ዓ.ም(አዲስ አበባ)
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የጸጥታና ኦፕሬሽን ዘርፍ ዘላቂ ሰላምን በከተማዉ ለማስፈን በማለም በ11ዱም ክፍለ ከተማ ለሚገኙ የሞተር ማህበር አመራሮችና አባላት በወንጀል መከላከልና መቆጣጠር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።
በስልጠናዉ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትል የቢሮ ሀላፊና የጸጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ ሀላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድር ሲሆኑ፤ በንግግራቸውም ሰላም የሁሉ ነገር መነሻ በመሆኑ ሰላምን ለማስፈን መተባበርና መደጋገፍ አስፈላጊ በመሆኑና የከተማው ህዝብ ካልተሳተፈ የጸጥታ መዋቅሩ ብቻዉን መስራት የማይታሰብና ዘላቂ ሰላም የሚሰፍነዉ በተለያየ ሙያ ዉስጥ ሆኖ በቅንጅት መስራት ሲቻል እንደሆነ በማዉሳት፤ከዚህ ቀደም በየ ዘርፍ ካለዉ የህብረተሰብ ክፍል ጋር በመሠራቱ በከተማዉ ትላልቅ ሽብሮች ማምከን ስለተቻለ የዛሬዉ ስልጠናም ግንዛቤ ፈጥሮ በጋራ የመስራትን ቅንጅት ለመጨመር ነዉ ሲሉ ገልጸዋል።
ስልጠናውን የሰጡት የአዲስ አበባ ፓሊስ ማህበረሰብ አቀፍ የጥናትና እቅድ ትንተና ዲቪዚዮን ሀላፊ ምክትል ኮማንደር ታዲዎስ አክሊሉ ሲሆኑ፤በወንጀል መከላከልና የሞተር ሳይክል አገልግሎት እንዲሁም ወንጀልን በመከላከል ስልት ዙሪያ በሰነድ መልክ ግንዛቤ ሰጥተዋል።
መድረኩን የመሩት አቶ ተስፋዬ ደንድር የቢሮዉ የጸጥታና ኦፕሬሽን ዘርፍ ሀላፊ፣ኢንስፔክተር ሰለሞን አዳነ የትራፊክ መምሪያና ህዝብ ግንዛቤ ዲቪዥን ሀላፊ እና ኮማንደር ገዛኸኝ ጌታነህ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የወንጀልና ትራፊክ አደጋ መከላከል ም/አዛዥ ሲሆኑ፤ስስቱም አወያዮች ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዉበታል።
መድረኩን ያጠቃለሉት አቶ ተስፋዬ እንደገለፁት ከማህበራቱ ጋር በስራ እለት ተእለት የምንገናኝ ቢሆንም በየጊዜዉ እንዲህ በስልጠና እና ዉይይት እየታገዙ መሄድ አስፈላጊ በመሆኑ ነዉ በማለት ገልጸዋል።
በስልጠናዉ ላይ አቶ ተስፋዬ ደንድር የቢሮዉ ምክትል የቢሮ ሀላፊ፣ ምክትል ኮማንደር ታዲዎስ አክሊሉ፣ አቶ ሀብታሙ ደረጄ የጉለሌ ክ/ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ሀላፊ፣ኢንስፔክተር ሰለሞን አዳነ የትራፊክ መምሪያና ህዝብ ግንዛቤ ዲቪዥን ሀላፊ፣ኮማንደር ገዘሃኝ ጌታነህ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የወንጀልና ትራፊክ አደጋ መከላከል ም/አዛዥ እና ከ11ዱም ክፍለ ከተሞች የተወጣጡ የአራት ማህበራት የሞተር ማህበር አመራሮችና አባላት ሲሆኑ በቀረበዉ የስልጠና ሰነድ ላይ በመመርኮዝ ጥያቄና አስተያየቶች ከተሳታፊዎች ተነስተዉ ምላሽና ማብራሪያ ከአወያዮቹ ተሰጥቶበት መድረኩ ተጠናቋል።በከተማዉ ዉስ ጥ 9 የሞተር ማህበራት ያሉ ሲሆን ለ ቀሪ 5ቱ ማህበራት በቀጣዩ ቀን እንደሚሰጥ በመድረኩ ተገል