የንቅናቄ መድረክ
"ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ቃል የንቅናቄ መድረክ ተካሄደ።
ህዳር 12/2018ዓ.ም (አዲስ አበባ)
****
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ 20ኛው የኢትዮጵያን ብሔር ብሔረሰቦች ቀንን አስመልክቶ ከማዕከል እስከ ወረዳ ለሚገኙ ሰራተኞች "ደሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ቃል ለሁለት ቀን የሚቆይ የንቅናቄ የስልጠና መድረክ ዛሬ በየካ ክ/ከተማ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ተጀምሯል።
ስልጠናውን የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የፀረ-ሙስና እና የስነ-ምግባር ዳይረክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰላም አምሳሉ ሲሆኑ፤ የስልጠናው አላማ ስለሚከበረው 20ኛው የኢትዮጵያን ብሔር ብሔረሰቦች መብት ማስከበር ቀን ቀደም ብሎ ማወቅና መረዳት ስላለበት መሆኑን ገልጿል።
ዳይሬክተሩ አክለውም ብዙኃነት መገለጫቸው ለሆነ ህዝቦች የዴሞክራሲ እና የፌዴራላዊ ሥርዐቶች አስፈላጊነት ብዙኃነትን ዲሞክራሲያዊ በሆነና አካታች በሆነ መንገድ ለማስተዳደር ነው ብለዋል።
የፈደራል ሥርዓት በውይይት፣ በምክክር እና በመደማመጥ ችግሮችን በመፍታት ዲሞክራሲያዊ የሆነ ህበረ ቢሄራዊ ለመገንባት የሚያስችሉ ተቋማት ማጠናከር፣ የአሰራር ሥርዓት መዘርጋት እና በአፈጻጸም የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን የፌደራል ሥርዓት በጠበቀ መልኩ መፍትሔ መስጠት እንደሚያስፈልግ አቶ ሰላም አምሳሉ ጠቅሰዋል።
የስርአቱ ተግዳሮቶች የዲሞክራሲና የፖለቲካ ባህል አለመዳበር ነው ያሉት አቶ ሰላም፣የፌደራል ሥርዓትን በህገመንግስታቸው ቢደነገጉም ብዙኅንነትን ዴሞክራሲያዊ በሆነ አግባብ መስተናገድ የሚሳናቸው ሀገራት መኖሩን እና በህገመንግስቱ የሚዳኙ መሆኑንም ገልጸዋል።
በመድረኩ ላይም ከማዕከል እስከ ወረዳ ያሉ ዳይሬክተሮች፣ አስተባባሪዎች፣ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች ተገኝቷል። መዱረኩ በነገውን ቀን ቀጥሎ ይውላል።