የሃይማኖትና የሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ የጥቅምት ወር የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ አካሄደ።
የሃይማኖትና የሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ የጥቅምት ወር የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ አካሄደ።
ህዳር 09/2018 ዓ.ም (ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)
*****
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የኃይማኖትና የሰላም ዕሴት ግንባታ ዘርፍ ከክ/ከተሞች ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት አስተባባሪዎችና ቡድን መሪዎች ጋር የጥቅምት ወር ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ አካሄዷል።
በግምገማው ወቅት በየክ/ከተሞቹ አስተባባሪዎችና ቡድን መሪዎቹ የተሰሩ ስራዎችና በሃይማኖት ተቋማት ላይ የመልካም አስተዳደር ችግሮች የመለየት ስራ እና የተወሰዱ መፍትሔዎችን በሪፖርት አቅርበዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ም/ል ቢሮ ኃላፊ ከቶ ብርሃኑ ረታ ክፍለከተሞች በሃይማኖት ጉዳዮች እና የሰላም ዕሴት ግንባታ ዘርፍ በማንኛውም ላይ ችግሮች ከመከሰታቸው በፊት የቅድመ መከላከል ስራዎች መስራት እንዳለባቸው ጠቅሰው፣ዘርፉ በዋናነት የሚሰራው፣የግንዛቤ እና ስልጠና መስጠት፣ፓናል ውይይትና ኮንፈረንስ ማካሄድ፣የብሔራዊ የወጣቶች በጎ ፈቃድ ላይ እና የሃይማኖት ተቋማት መደገፍ መከታተል እርስ በእርስ ያላቸው መስተጋብር እንዲጠናከር እና መረጃዎችን የመሰብሰብ ስራ እና ትኩረት የሚሹ እንደሆኑም ገልጸዋል።
ከብሔራዊ በጎ ፈቃድ ጋር በተያያዘ የክ/ከተማና የወረዳ አመራሮችን ባለቤት በማድረግ መስራት፣ወጣቶች ላይ የአመለካከትና ክህሎት ላይ መስራት፣አመቻቾች ላይ ትኩረት ማድረግ፣የሃይማኖት ተቋማት ላይ ያሉ ችግሮችን መፈተሽና ችግሩን መፍታትና ዕምነት ተቋማትን ሰላማዊነት ማስቀጠል ላይ ሀላፊው የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫ ሰጥቷል።