ጨለማን ተገን በማድረግ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ለመ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

ጨለማን ተገን በማድረግ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ለመከላከል የመንገድ ዳር መብራቶች ማብራት

ጨለማን ተገን በማድረግ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ለመከላከል የመንገድ ዳር መብራቶች ሚና ጉልህ መሆኑ ተገለፀ።

ህዳር 8/2018 ዓ.ም (ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)

*****

ከዚህ በፊት ከፍተኛ የፀጥታ ስጋት የነበሩና ጨለማን ተገን በማድረግ ሃንግ ዝርፊያና ንጥቂያ የሚፈፀምባቸው የነበሩ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 በተለምዶ አቡነ ጎርጎርዮስ ቤተክርስቲያን አካባቢና በወረዳ 4 ጎተራ ኮንዶሚኒየም የመብራት ማብራት ስራ ጉብኝት ተደርጓል።

በጉብኝቱ ላይም የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ሲሆኑ በንግግራቸውም ከተማችን አዲስ አበባ ሰላሟ የተረጋገጠ ዜጎቿ 24ሰዓት ወጥተው በሰላም የሚገቡባት የከተማችን ልማት እየተፋጠነ እምርታ የሆነ ውጤት ያስመዘገብንበት፣ህዝቡን የሰላም ባለቤት አድርገን በመስራታችንና ሲሆን ለዚህም የከተማችን የጀርባ አጥንት የሆኑ የሰላም ሰራዊት አባላት ወንጀል የሚከሰትባቸው ቦታዎችን በመለየት መረጃዎችን ለፀጥታ አካላት ጥቆማ በማድረግ ወንጀልን በጋራ ለመቀነስ ተችሏል ብለዋል።

ኃላፊዋ አክለውም በዛሬው ዕለት ወንጀል ከመቀነስ አኳያ ህዝቡን ያሳተፈ ስራ በመስራት ወንጀል የሚካሄድባቸውን አከባቢዎች በመለየት ማህበረሰቡን በማወያየት ሚናውን እንዲወጣ በማድረግ ሁሉም ማህበረሰብ በተለይ ጭለማ የሆኑ ቦታዎች መብራት እንዲወጣ መደረጉም ገልጸዋል።

የዛሬው ጉብኝት 5ኛ ክ/ከተማ የሆነው ቂርቆስ ክ/ከተማ ሲሆን፣ሌሎች ክ/ከተሞችም ይሄንን ልምድ ወስደው ማስቀጠል እንዳለባቸው ጠቅሰው፣ይህ ክ/ከተማ ትላልቅ የንግድ እንቅስቃሴዎች የሚካሄድበት ከ/ከተማ እኝደመሆኗ መጠን የፀጥታ አካላቶችና ሌሎችም በመቀናጀት የጨለማን ቦታዎችን መብራት የወጡበትን መንገዶችን የምንመለከትበትና በአራት ወር ውስጥ የተሰሩ ስራዎችን የምንገመግምበት ነው ብለዋል።

የቂርቆስ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ምስክር ነጋሽ በጉብኝቱ ተገኝተው እንደተናገሩት፣በከተማችን የሚካሄዱ ልማቶችና ፕሮጀክቶች እንዲሁም 24 ሰዓት የሚካሄደው ንግዶች በከተማዋ አስተማማኝና ዘላቂ ሰላማሟን ማስፈን ስለተቻለ እና በዛሬው ዕለት ጨለማ በሆነ አከባቢና ብሎኮች መብራት በማስወጣት የአከባቢያቸውን ሰላም ማስጠበቅና የሚፈጸሙ ወንጀሎችን መቀነስ እንደተቻለም ገልጸዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን በየክ/ከተሞች በአራት ወራት ውስጥ የተሰሩ ስራዎች ሪፖርት የቀረበ ሲሆን ከተሳታፊዎች አስተያየቶች ቀርቦ ሰፊ የሆነ ውይይት ተደርጓል።

በመጨሻም የህብረተሰብ ተሳትፎ የአንበሳውን ድርሻ ወስዶ በማጎልበት የውስጥ ለውስጥና የመንገድ ዳር መብራቶችን በመቀናጀት ማስወጣት፣ዕቅድ ከልሶ ያልተሰሩ ስራዎችን ሰርቶ ወደሌላ ስራ መግባት የተዘረጉ መሰረተ ልማቶችን ከስርቆት በመጠበቅ የከተማችንንዘላቂ ሰላም ማስጠበቅ እንደሚቻልም አሳስበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፣የቂርቆስ ክ/ከተማ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ምስክር ነጋሽ፣የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ መምርያ ም/ል ጠቅላይ አዛዥ ኮሚሽነር ፍቅሩ አለማየሁ፣የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ ስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እና የከተማና የክ/ከተሞች ከፍተኛ አመራሮች፣በጉብኝቱ ላይ ተሳትፈዋል።