በሰላምና በሀገር ግንባታ ዙሪያ ከአረጋውያን ማህበር ጋር የተካሄደ ውይይት
በሰላምና በሀገር ግንባታ ሂደት ሀገራዊ /ብሔራዊ/ ጥቅምን በማጠናከር ረገድ ማህበራት እያደረጉት ያለውን ተግባር አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ ቀረበ።
ህዳር 8/2018 ዓ.ም (ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)
*****
የዕድር ምክር ቤት አመራሮች፣አረጋውያን ማህበርና የሀገር ሽማግሌ በሰላምና በሀገር ግንባታ ሂደት ሰላምን በማስፈን ረገድ እያደረጉት ያለውን ተግባር አጠናክረው እንዲቀጥሉ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ም/ል ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ረታ ጥሪ አቀረቡ፡፡
የሀገራችንና የከተማችን በሀገረ መንግስት ግንባታና ሰላም ግንባታ አስተማማኝ እና ዘላቂ በማድረግ ረገድ የዕድር ምክር ቤት አመራሮችና አረጋውያን ማህበር ሚና የማይተካ እንደነበር በማስታወስ፣ ይህንኑ ተግባራቸውን አጠናክረው መቀጠል እንደሚጠበቅባቸው አመላክተዋል።
ሀላፊው አክለውም የሀገራችንን ሰላምና ልማት ለማስቀጠል መንግስት ብቻውን መወጣት እንደማይችል ጠቁመው፣ሲቪክ ማህበራት፣የብዙኃን ማህበራት እና ሚዲያዎች ህዝቦችን በማቀራረብ አንዱ ወደ አንዱ ትስስር እንዲጎለብት በአውንታዊ መንገድ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ አሳስበዋል።
አቶ ታዬ የቂርቆስ ክ/ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ሀላፊ በበኩላቸው የከተማችን ልማት ዕለት ከዕለት በተጨባጭና የሚታዩ ለውጦችን እያስመዘገበች እንደሆነች ጠቅሰው፣ይህንን ልማት ለማስቀጠል የሀገር ሽማግሌዎችና አባቶች፣የከተማችን የዕድር ምክር ቤት አመራሮች ሁሉም የሚመለከተው አካላት ሰላም በማስጠበቃቸው እንደሆና፣ቀጣይም ይህንን ሚናቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።
በሀገረ መንግስትና ሰላም ግንባታን የሰላምና የመቻቻል እሴቶችን፣ብሔራዊ ጥቅሞቻችንን ለማጎልበት የሚያግዝ ሰነድ በአቶ ኤሊያስ ቀጀላ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር የኃይማኖትና የሰላም ግንባታ ዘርፍ የስልጠና ቡድን መሪ የሆኑ በመድረኩ አቅርበዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የኃይማኖት ጉዳዮችና የሰላም ግንባታ ዘርፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን እንየው እንዳሉት ሀገራችን ኢትዮጵያ ረጅም ታሪክ ያላት ሀገር እንደመሆኗ መጠን፣ብሔራዊ ጥቅሞቻችንን ማለትም የህዳሴ ግድብን ሁሉም ዜጎች ባደረጉት አስተዋጽኦ እንደሆነ አንስተው፣አሁን ላይ የተጀመረው የባህር ወደቡንም እሀውን ለማድረግ በሀገረ መንግስትና ሰላም ግንባታ ላይ አጠናክሮ ማስቀጠል አለባቹ ሲሉ መድረኩን ባወያዩበት ወቅት ተደምጠዋል።
በማጠቃልያቸው አቶ ብርሃኑ ረታ እንዳሉት፣ኢትዮጵያ ብዙ ሀብቶችን የያዘች፣ብዙኃነቶችን ያቀፈች ሀገር ስትሆን፣ገዢ ትርክት ላይ ማዕከላዊ አድርገን ሰላምን፣ሀቅንና እውነትን ይዘን፣በየአከባብያችን ጨለማ ቦታዎች ወደ ብርሃን በመቀየር ጨለማን ተገን አድርጎ ወንጀል የሚፈጽሙትን በመቀነስ፣የቅጥር ጥበቃ የሚያስፈልገው ላይ ቅጥር ጥበቃ መቅጠር፣በ8882 ላይ ነጻ የስልክ መስመር በመጠቀም መረጃ መስጠት፣ያላቹን ዕውቀት ጥበብ በመጠቀም በአከባቢያቹ የሰላም አባሳደር ሆናቹ ትውልድ ላይ መስራትና የውስጥ ትስስርን የማጎልበት ሚናቹን እንድትወጡ ሲሉ አደራ ጭምር አሳስበዋል።
በመጨረሻም በቀረበው ሰነድ ላይ ተሳታፊዎች የተለያዩ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ቀርበው፣መድረኩን ያወያዩ አወያዮች ማብራርያ ሰጥተዋል።
በመድረኩም የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ም/ል ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ረታ፣የቂርቆስ ክ/ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት አቶ ታዬ የማዕከልና የክ/ከተማ ዳይሬክተር፣አስተባባሪዎችና ቡድን መሪዎች፣ የከተማው ዕድር ምክር ቤት አመራሮችና አረጋውያን ማህበር ተገኝተዋል።