ወንጀልንና ድንገተኛ አደጋን ቀድሞ መከላከል

image description
- recent news   

ወንጀልንና ድንገተኛ አደጋን ቀድሞ መከላከል

ወንጀልንና ድንገተኛ አደጋን ቀድሞ በመከላከል የከተማውን ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ እንደሚገባ ተገለፀ ።

ህዳር 6/2018 ዓ.ም(ሰ.ፀ.አስ. ቢሮ)
       ****
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የጸጥታና ኦፕሬሽን ዘርፍ ከሁሉም ክ/ከተማ ለተወጣጡ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ማህበረሰብ አቀፍ የጸጥታ አጠባበቅና ወንጀል መከላከል ኦፊሰሮች እንዲሁም ለአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋ መከላከል ባለሙያዎች በወንጀል መከላከል ስልት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አዘጋጅቷል።

በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ላይ በመገኝት መልዕክት ያስተላለፉት አቶ ተስፋዬ ደንድር የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ እንዳሉት አለም በፈጣን እድገት ላይ ካለችበት ሁኔታና ከቴክኞሎጂዎች አብሮ መፈጠር ጋር ተያይዞ ወንጀሎች የሚፈጸሙበትና የሚከናወኑት ኢደት እጅግ ፈጣንና አዳጋች እንደመሆናቸው መጠን እንደ አሁን ቀደሙ ባለበት መንገድ ድርጊቶች አብረው ስለማይኔዱ ዲጂታል አለምን በመጠቀም በርካታ ወንጀሎች በከተማው ላይ እየተፈጸሙና ወንጀሎቹ ውስብስብ ከመሆኑ አንጻር ስልቱ እረቂቅ ነው በማለት የገለፁት ሀላፊው 

ግንዛቤ መፍጠር የተፈለገው የከተማውን ሰላም ለማስጠበቅ ቀድሞ ወንጀልን በመከላከል በመቆጣጠር ላይ የከተማው አመራር የጸጥታ አካላት አጋዥ ሀይሎች በከፍተኛ ሁኔታ እየሰሩና ድርጊቱን ለመቀነስ እንደሚገኙም ጠቅሰው ሁል ግዜም በማንኛውም ሰአት ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ አጠንክሮ በማስቀጠል ከችግሩ መላቀቅ ይገባናል ሲሉ ተናግረዋል።

ሀላፊው አያይዘውም ህጋዊ ባልሆነ የአሰራር ስልት ህገ ወጥ ድርጊቶች እየተፈጠሩ ስብህና እየጠፋ ስለመጣ ወንጀልን ቀድሞ በመከላከል ላይ ንቁ ሆኖ የስጋት ቦታን መለየት ማን ምን እያከናወነ እንደሆነ እይታን ማስፋት ትልቁና ዋናው ስራችን በማድረግ የትኩረት እይታን ቀድሞ በመለየት አሁን ላይ ከምንሰራው ስራ በበለጠ መልኩ ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት በማድረግና በማሳተፍ በማስተባበር አደጋንና ወንጀልን በመከላከል በመቆጣጠር ለከተማው ሰላም በጋራ መትጋት እንደሚገባ አሳስበዋል።

ስልጠናው የሰጡት ም/ኮማንደር ታዲዎስ አክሊሉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ማህበረሰብ አቀፍ ጥናትና ዕቅድ ትንተና ዲቪዚዩን ሀላፊ ሲሆኑ ዘመናዊ ወንጀል መከላከልና መቆጣጠር፣ወንጀልና የወንጀል ባህሪይ ድርጊቱና አሳሳቢነቱ ሁኔታዊ ወንጀል መከላከል ቴክኖሎጂ እና ወንጀል መከላከል በወንጀል መከላከል ውስጥ ቁልፍ ባለ ድርሻ አካላት ስላላቸው ሚና በተመለከተ ገለፃ አድርገዋል።

ስልጠናው መነሻ በማድረግ ከተሳታፊዎቹ ለተነሳው ሀሳብና አስተያየት ሀላፊዎቹ ምላሽና ማብራሪያ በመስጠች መድረኩ ተጠናቋል ።

በስልጠናው ላይ አቶ ተስፋዬ ደንድር የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ፣ኢንስቴክተር ባህሩ ኡርጌ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አግልግሎት ጽ/ቤት ሀላፊ
የሁሉም ክ/ከተማ የተወጣጡ የአዲስ አበባ ፖሊስ ማህበረሰብ አቀፍ የጸጥታ ፖሊስ ወንጀል መከላከል ኦፊሰሮች የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋ መከላከል ባለሙያዎች የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ የማዕሰል ባለሙያዎችና የክ/ከተማ የዘርፉ አስተባባሪዎች ተገኝተዋል።