የመርካቶ የግብይት ስርአት በህግ አግባብ

image description
- recent news   

የመርካቶ የግብይት ስርአት በህግ አግባብ

የመርካቶ የግብይት ስርአት በህግ አግባብ እንዲመራ እየተደረገ መሆኑ ተገለፀ።

ህዳር 5/2018 (አዲስ አበባ)
****

በሀገሪቱና በከተማችን አዲስ አበባ የሚገኘው ግዙፉ የገበያ ማዕከል መርካቶ የንግድ ስርአቱን ህግና ስርአት ለማስያዝ በከተማ ደረጃ ግብረሃይል ተቋቁሙ እየሰራ የሚገኝ ሲሆን በዛሬው ዕለትም እስከአሁን የተሰሩ ስራዎችን በመገምገም ቀጣይ የስራ አቅጣጫ ተቀምጧል።

ግምገማውን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ሲሆኑ ግብረ ሃይሉ በዋነኛነት መንገድ በመዝጋት ንግድ የሚፈፅሙ፣ የ‍ኣለንግድ ፈቃድ የሚሰሩ፣ ደረሰኝ የማይቆርጡ፣ በኮንትሮባንድና በኢ-መደበኛ ንግድ ላይ በተሰማሩ ነጋዴዎች ላይ ህግና ስርአትን የማስከበር ተግባር እያከናወነ መሆኑን  አንስተዋል።

ኃላፊዋ አያይዘውም ህግ ከማስከበሩ ጎን ለጎን በኢ-መደበኛ የንግድ ስርአት ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎችን በቀጣይ ከመርካቶ ውጪ ባሉ ቦታዎች ላይ ህጋዊ የስራ እድል እንደሚመቻችላቸው ገልፀዋል።

 ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ አክለዉም የመርካቶ የገበያ ስርአት ህግን ተከትሎ እንዲመራ እየተደረገ ያለው ሂደት ውጤት እያስገኘ መሆኑን ገልፀው፤ በቀጣይም ህግና ስርአትን ተከትለው በማይሰሩ፣ የዋጋ ንረት በሚፈጥሩ፣ ያለንግድ ፈቃድ በሚሰሩ፣ ያለደረሰኝ ንግድ በሚያከናዉኑ፣ በህገ ወጥ የገንዘብ ዝዉዉር ላይ ተዋናይ በሆኑ፣ ምርት በሚደብቁና በኮንትሮባንድ ንግድ ላይ በተሰማሩ ነጋዴዎች ላይ ተመሳሳይ እርምጃዎችን በመውሰድ ወደህጋዊ የንግድ ስርአቱ የማስገባቱ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ዋና ስራአስፈፃሚ አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ በበኩላቸው ኢ-መደበኛ የንግድ ስርአትን ህግና ስርአት ለማስያዝ እየተሰራ ያለው ስራ ውጤታማ መሆኑን ገልፀው በዘርፉ ተሰማርተው የነበሩት አካላትም በቀጣይ ህግን ተከትለው የሚሰሩበት ስርአት መዘርጋቱን አንስተዋል።

በመድረኩ ላይ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ፤ አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ዋና ስራ  አስፈፃሚ ፤ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ፤ አቶ ተስፋዬ ደንድር የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊን፣ ኮሚሽነር መኮንንና ኮማንደር ገዛኧኝ የአዱስ አበባ ፓሊስ አመራሮች ጨምሮ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።