የፓርኪንግና የታክሲ ተራ አስከባሪ ተወካዮች ጋር በጸጥታ አጠባበቅ ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።
በከተማው ላይ ከሚገኙ የፓርኪንግና የታክሲ ተራ አስከባሪ ተወካዮች ጋር በጸጥታ አጠባበቅ ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።
ህዳር 5/2018 ዓ.ም(ሰ.ፀ.አስ. ቢሮ)
****
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ከሁሉም ክ/ከተማ ከተወጣጡ የፓርኪንግና ተራ አስከባሪ ሀላፊዎች ጋር በከተማው ላይ በጸጥታ ጉዳዩች ዙሪያ ስለሚኖራቸው ተሳትፎ ዙሪያ የውይይት መድረክ አካሂዷል።
በውይይቱ ላይ በመገኘት መድረኩን የመሩት አቶ ፍስሐ ጥበቡ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ እንዳሉት የማህበራቱን አሰራር የተሻለና የተቀላጠፈ ለማድረግ በአዲስ አሰራር ወደ ስራ መገባቱን አስታውሰው እንደ አዲስ ማቋቋምም የተፈለገው ስራ አጥ ለሆኑ ወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር በተለይም ህብረተሰቡ በየግዜው የሚያነሳውን እሮሮ ለመቀነስ ታስቦ ነው ያሉት ሀላፊው
አሁንም ግን ያልተቀረፉ በርካታ ችግሮች እንዳሉና ህብረተሰቡ የሰጠውን ሀላፊነት በአግባቡ በመጠቀም ለህብረተሰቡ ተገቢውን ክብር በመስጠት ተገቢ ያልሆኑ አላስፈላጊ የሞያ ስነምግባሮችን በመቅረፍ ተገቢውን አግልግሎት መስጠት እንደሚገባም ገልጸዋል።
ሀላፊው አያይዘውም ማንኛውም ነገር ዘላቂ የሚሆነው የችግሩን መፍቻ ሲታወቅ ለችግሮቹ መፍቻ ህጋዊ መንገድ መጠቀምና መግባባት ያስፈልጋል በማለት ከተማዋ በለውጥ ጎዳና ላይ እንደመሆኗ መጠን ወደ ዘመናዊነት ወደ መሰልጠን የተሻገርን ስለሆንን ከተማውን የሚመጥን ስራ መስራት ያስፈልጋል በማለት የጋራ የሆነውን ሀገርና ከተማ በጋራ በመጠቀም በሀሳቦች ላይ በጋራ በመግባባት ሀገርን መቀየር እንደሚያስፈልግ በመግለፅ የስራ ስምሪታችን ቢለያይም የምናገለግለው ሀገርን እንደመሆኑ መጠን ችግሮቻችንን በጋራ በመፍታት ከጸጥታው አጋዥ ሀይሎች ጋር በመተባበር የጸረ ሰላም ሀይሎችን ሴራ በማክሸፍ እንዳሁን ቀደሙ በትብብር በመስራት አሁንም አልፎ አልፎ የሚከሰቱ የወንጀል ድርጊቶች መቆጣጠር ይገባል ሲሉ አጽንኦት ሰተው ተናግረዋል ።
በመጨረሻም ማንኛውም ወንጀል ነክ የሆኑ ጉዳዮች ሲያጋጥሙ በነጻ የስልክ መስመር በ8882 ነጻ የስልክ መስመር በመጠቀም ጥቆማ መስጠት እንደሚገባ አሳስበዋል።
አቶ ውድነህ አቢ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ባለሙያ ሲሆኑ ማህበራቱ ስላላቸው ሚና፣ሀላፊነትና ተግባር በአግልግሎት ወቅት ስለሚታዩ ችግሮችና ክፍተቶችንና በቀጣይ መስራት ስለሚገባቸው ጉዳዩች ላይ መነሻ ጽሁፍ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ከተደረገ በሏላ ሀላፊው በመድረኩ ላይ ለተነሳው ሀሳብና አስተያየት ምላሽ በመስጠት ውይይቱ ተጠናቋል።
በውይይቱ ላይ አቶ ፍስሐ ጥበቡ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ፣የሁሉም ክ/ከተማ የዘርፍ አስተባባሪዎች ተራ አስከባሪዎችና የፓርኪንግ ማህበራት ተወካዮች ተገኝተዋል።