ቢሮው ከባለድርሻ አካላት ጋር የአንደኛ ሩብ ዓመት ቅንጅታዊ ስራዎች ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ገመገመ።
ቢሮው ከባለድርሻ አካላት ጋር የአንደኛ ሩብ ዓመት ቅንጅታዊ ስራዎች ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ገመገመ።
ጥቅምት25/2018ዓ.ም
*****
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የቅንጅታዊ ስራዎች ዕቅድ አፈጻጸም ገምግሟል።
በግምገማው ወቅትም የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ የቢሮው ም/ል ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሀኑ ረታ ሲሆኑ በንግግራቸውም የዛሬው መድረክ አሁን በነበረን መንገድ አፈጻጸም መገምገም በአዲሱ መዋቅር የህግና ፍትን ማስከበር የክላስተሩ አስተባባሪ ሆኖ የሚሰራ ሲሆን ከኛ ምን ይጠበቃል የሚለውን የምናይበት መድረክ እንደሆነ ጠቅሰው፣በዋናነት የህዝብ ደህንነትና ሰላም ማስጠበቅ፣ወንጀል መተላለፍና ህገ ወጥ ተግባራትን መከላከል፣የዜጎች ፍትህና መብት መጠበቅ እና የአደጋ ጊዜ ዝግጅት የክላስተሩ ዋና ዋና ተልዕኮዎች እንደሆኑ ገልጸዋል።
የተቋማት ቅንጅታዊ አሰራር አስፈላጊ ነው ያሉት ሀላፊው አቶ ብርሀኑ ረታ አለም አቀፍ እና አህጉራዊ የአደባባይ በዓላትና ኩነቶች ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ መከበራቸውንና ከተማችን ሰላም ያላት ከተማ እንድትሆን በቅንጅት በመሠራታቸው የመጣ ውጤትና ማሳያ እንደሆነም አንስተዋል።
ለግምገማው የሚሆን መነሻ ሰነድ ያቀረቡት የቢሮው አማካሪ የሆኑ አቶ ገብሬ ዳኘው ሲሆኑ ሰነዱን ባቀረቡበት ወቅት፣የህግና መልካም አስተዳደር ክላስተር የሚቀናጅባቸው ዋና ዋና አገልግሎቶች፣በክላስተር ተቋማት መካከል ቴክኒካዊ ትብብርና መግባባት እንዲፈጠር የሚያደርግ ክላስተሩ ውጤታማ እንዲሆን አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን አሰራሮችን የመለየት ተግባራዊ እንደሚያደርግና ግንዛቤ እንደሚፈጥርም በሰነዱ አብራርተዋል።
በመጨረሻም በመድረኩ የተገኙ ተሳታፊዎች የተለያዩ አስተያየቶችና ጥያቄዎች አንስተው፣መድረኩን የመሩት የቢሮው አመራሮች ማብራርያና ምላሽ ሰጥተዋል።
በመድረኩም የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ም/ል ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ረታ፣አቶ ገብሬ ዳኘው የቢሮ አማካሪ፣የቢሮ ዳይሬክተሬቶችና ከከተማ አስተዳደር ካሉ ተቋማት የተወጣጡ ኃላፊዎችና ተወካዮች ተገኝተዋል።