የምደባ ኮሚቴው የመረጃ ጥራት ላይ እና ደንብ 1...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የምደባ ኮሚቴው የመረጃ ጥራት ላይ እና ደንብ 156/2016 ላይ ትኩረት በማድረግ ሊሰራ ይገባል።

የምደባ ኮሚቴው የመረጃ ጥራት ላይ እና ደንብ 156/2016 ላይ ትኩረት በማድረግ ሊሰራ ይገባል።

አቶ ተስፋዬ ደንድር የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ

****

ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም (አዲስ አበባ)

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ እየሰራ ላለው ተቋማዊ ሪፎርም በማእከል እና በክ/ከተማ ያዋቀራቸው የምደባ ኮሚቴዎች የደረሱበትን የስራ ሂደት በዛሬው ዕለት ገምግሟል።

መድረኩን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድር የምደባ ኮሚቴው የመረጃ ጥራት እና የመረጃ አደረጃጀት ላይ ትኩረት አድርገው መስራት እንደሚገባቸው ጠቁመዋል፡፡

ኃላፊው አክለውም ለሰራተኛው የተሰጠው የፈተና ውጤት ይፋ እስኪደረግ ድረግ የሰራተኛውን መረጃ ማደራጀትና ቅድመ ዝግጅቶችን ማጠናቀቅ እንደሚገባ ጠቁመው፤ ለምደባ ኮሚቴው መሟላት ያለባቸው ከምቹ ሁኔታ መፍጠር ጀምሮ እንዲሁም የኮሚቴው የስራ ሂደት ላይ የሰራተኛ የግል ማህደር በጥንቃቄ መያዝ እንዲሁም የስራ ዲሲፕሊን ላይ ከፍተኛ ትኩረት በማድረግ ስራውን በጥራትና በተያዘለት የጊዜ ገደብ ማጠናቀቅ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

በማእከልና በ11ዱም ክ/ከተሞች ላይ የተሰሩ የቅድመ ስራዎችን በመገምገም ቀጣይ መሰራት ያለባቸው ተግባራት ላይ አቅጣጫ ተቀምጧል፤

በመድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድርን ጨምሮ በማእከልና በክ/ከተማ የሚገኙ የምደባ ኮሚቴ አባላት ተገኝተዋል፡፡