ቢሮው ለሰላም ሰራዊት አባላት የምስጋና መርሐ ግ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

ቢሮው ለሰላም ሰራዊት አባላት የምስጋና መርሐ ግብር አካሄደ።

ቢሮው በ2018 ዓ.ም የመስቀልና ኢሬቻ በዓላት በሰላም እንዲከበሩ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የሰላም ሰራዊት አባላት የምስጋና መርሐ ግብር አካሄደ።

ጥቅምት 13/ 2/2018 ዓ/ም(አዲስ አበባ )

**

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ በ2018 ዓ.ም የመስቀልና ኢሬቻ በዓላት በሰላም እንዲከበር አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት የምስጋና መርሐ ግብር አካሂዷል።

በመርሐ ግብሩ ላይ በመገኝት የእንኳን ደህና መጣችሁና ፕሮግራሙን አስመልክቶ መልዕክት ያስተላለፍት ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ እንዳሉት

ከተማችን አዲስ አበባ በከፍታና በማንሰራራት በለውጥ ጎዳና ላይ እንደምትገኝና ለዚህም ማሳያ የሆኑት የህዳሴ ግድብ ትሩፍቶቻችን የሆኑትና እንደ ሀገርም በተሰራው ስራ መላው የከተማው ከፍተኛ አመራሮች፣ነዋሪዎች የጸጥታ አካላት የሰላም ሰራዊት አባላት የሀገራችን ሉአላዊነት ታሪክ የተበሰረበት መሆኑን አስታውሰው

ቢሮው በአዋጅ በተሰጠው ስልጣንና ሀላፊነት መሰረት በርካታ አደረጃጀቶችን በመፍጠር በከተማው የታቀደውን የሽብር የሀይል ጥቃት እንዲከሽፍ ከማድረግም በላይ ከተማው ላይ የሚከናወኑ በርካታ በዓላት፣ኮንፈረንሶችና ትላልቅ ጉባኤዎች በሰላም እንዲከበሩ መላው የከተማው ነዋሪ፣የጸጥታ አካላት የሰላም ሰራዊትና የጸጥታ አካላት በቅንጅት በመሆን ላበረከቱት አስተዋጽኦ በቢሮው በራሴና በከተማው አስተዳደር ስም ምስጋናን አቀርባለው ሲሉ ሀላፊው የተደመጡ ሲሆን

የከተማውን ሰላም አስተማማኝ በማድረግ የህብረተሰቡን ሰላም በማስጠበቅ አደረጃጀቶችን በመፍጠር ነዋሪው ሰላሙ እንዲረጋገጥ በጸጥታ ስራችን ላይም በመሳተፍ የህግ ማዕቀፍም በመስራት አይተኬ የሌለው ስራም እየተሰራና እየተሰራም ያለው ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ክብርት ሊዲያ ግርማ በንግግራቸው አውስተዋል

ክብርት ሀላፊዋ አያይዘውም ለሰላም መረጋገጥ በልዩ ሁኔታ በመደገፍ በዘላቂነት ከተማ አስተዳደሩ እየሰራ ይገኛል ያሉት ክብርት ሊዲያ የሰላም ሰራዊት አባላትን በየግዜው በማነቃቃት አለኝታም በመሆን ለሰላም በመትጋት የከተማውን ህዝብም ተሳታፊ በማድረግ በትኩረት እየተሰራ በሚገኝበት መዋቅር ተሳታፊ በመሆን ሰላምን አደጋ ላይ ለመጣል የሚሰሩ በርካታ አካላት እንዳሉ አስታውሰው

ወቅቱ አንድነትን የሚጠይቅ እንደመሆኑ መጠን ለሀገር እና ለሰላም አበክሮ በመስራት በቀጣይም በጋራ በመስራት ሁሉም የበኩሉን ሀላፊነት እንዲወጣ አደራ እላለው በማለት በአክብሮት ተናግረዋል።

መርሃግብሩን በመክፈቻ ንግግር የከፈቱት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊና የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ፍስሃ ጥበቡ ሲሆኑ፤በንግግራቸዉም የሰላም አምባሳደር የሆናችሁ የሰላም ሰራዊት አባላት

የ2018 ዓ.ም የመስቀልና የኢሬቻ በዓላት ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲጠናቀቁ ያለምንም ክፍያ ቁርና ዝናቡን ችላችሁ ከአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ መዋቅር ጋር ተባብራችሁ ለዛሬ ስላበቃችሁን እናመሰግናለን በማለት ለሰላም ሰራዊት አባላቱ ምስጋናን ችረዋል።

የእለቱ የክብር እንግዳ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋዉ የአዲስ አበባ ከተማ ፓሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ

አህጉራዊ ከተማዊ ትልልቅ ሁነቶች ያለ ምንም ኮሽታ እንዲከበሩ በብዙ ለውጦች ዉስጥ የምትገኘዉ ከተማችን አዲስ አበባ ልማታችን እንዲቀጥል የጸጥታ ሀይሉና የሰላም ሰራዊቶች ከአመራሮች ጋር ተናበን በመስራታችን እጅ ለእጅ ተያይዘን ፀጉረ ልዉጦችን በመለየት ለጸጥታ አካላት አሳልፎ በመስጠት የመረጃ ምንጭ በመሆን የተለያየ ችግር ፈጥረዉ ከተማችችንን መሸሸጊያ ለማድረግ የሚመጡ አካላትን በመዋጋት በጀመርነዉ መንገድ ከተማችንን እንድንጠብቅ በማለት በአደራ ጭምር መልእክት አስተላልፈዋል።