ከተማ አቀፍ ኮንፈረንስ
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሃገር በቀል የሰላምና መቻቻል ዕሴቶች ለትውልድ ግንባታ ያላቸው ፋይዳ በሚል ርዕስ ከተማ አቀፍ ኮንፈረንስ አካሄደ ።
ጥቅምት 11/ 2/2018 ዓ/ም (አዲስ አበባ)
**
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የከተማውን ሰላም ለማረጋገጥና አስተማማኝ ለማድረግ በርካታ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ የሚታወቅ ሲሆን በዛሬው ዕለትም ሃገር በቀል የሰላምና መቻቻል ዕሴቶች ለትውልድ ግንባታ ያላቸው ፋይዳ በሚል ርዕስ በከተማው ውስጥ ከሚገኙ ከሁሉም ክ/ከተማ ከተወጣጡ ሴት ተወካዮች ጋር ውይይት አድርጓል።
በኮንፈረንሱ ላይ በሀገር በቀል የሰላምና መቻቻል ዕሴቶችን ለትውልድ ግንባታ ስላላቸው ፋይዳ በተመለከተ መነሻ ጹሁፍ ያቀረቡት ዶክተር ታምሩ ፈይሳ በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ መምህርና ተመራማሪ ሲሆኑ መነሻ ጹሁፉን ባቀረቡበት ወቅት የሰላም መቻቻል ባለበት ሀገር ውስጥ ሰላም ያለው ፋይዳ እጅግ የጎላ መሆኑን ጠቅሰው በትውልድ ቅብብሎሽ አንድ የሆነች ሀገር እንደሆነችም አስታውሰ ሀገር በቀል እሴቶችን የጋራ መሆናቸውን በመረዳት ለትውልዱ በማስተላለፍ ሀገር ማንነት ጠብቆ የሴቶችም ሚና የጎላ በመሆኑ የመቻቻልን እሳቤ በማስተላለፍ ሰላምን ማስቀጠል እንደሚገባ በሰነዱ ጠቅሰዋል።
ትውልድን መስመር ማስያዝ የሚቻለው ያሉትን ሀገር በቀል ሁነቶች አጠናክሮ በማስቀጠልና ትዉልዱም ላይ ተረባርቦ በመስራት ለውጥ እንደሚያመጣና የሚፈጠሩ ተግዳሮቶችን በበቂ ሁኔታ በማለፍ በቀጣይ መንግስት፣ህብረተሰቡ ት/ቤቶች የሰላም ክበባት፣ሚዲያዎች አንድነትና መተባበርን የሚያውጁ ፕሮግራሞች መስራት ይጠበቅብናል ሲሉ ወ/ሮ የሺ ወልዴ ገልፀዋል ።
በመጨረሻም ከተማችን ላይ አስተማማኝ ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት በተማችን የሚንቀሳቀሱ የጥፋት ኃይሎችን በመከታተል የልማት ስራ የመልካም አስተዳደር ስራ ላይ ተሳትፎዎቻቹን በማድረግ ውይይታቹን በማድረግ በማድበር የሰላምና ፀጥታ መረጃዎችን በመስጠት ሚናቹን መወጣት አለባቹ ሲሉ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በማጠቃለያቸው አሳስበዋል።
በመድረኩም የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፣ም/ል ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ረታ፣የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሴት አደረጃጀት አማካሪ ወ/ሮ የሺ ወልዴ፣በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪ ዶ/ር ታምሩ ፈይሳ፣ከአስራንዱም ክ/ከተሞች የተወጣጡ ሴት አደረጃጀቶች ተገኝተዋል።