ቢሮው የስታንዳርዳይዜሽን አገልግሎት አፈጻጸም...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

ቢሮው የስታንዳርዳይዜሽን አገልግሎት አፈጻጸም ገመገመ።

የቢሮው የስታንዳርዳይዜሽን አገልግሎት ዝግጅት ክትትልና ምዘና ክፍል በአንደኛ ሩብ አመት ውስጥ የተሰሩ ስራዎችን ገመገመ።

ጥቅምት 11/2018 ዓ/ም (አዲስ አበባ )

**

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የስታንዳርዳዜሽን አገልግሎት ዝግጅት ክትትልና ምዘና ክፍል በመልካም አስተዳደርና የቅሬታ አቤቱታ ዙሪያ በአንደኛ ሩብ አመት ውስጥ የተሰሩ ስራዎችን ከባለድርሻ አካላትና ሲቪክ ማህበራት ጋር ውይይት አድርጓል።

በአንደኛ ሩብ አመት ውይይቱ ላይ በመገኝት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት አቶ ብርሀኑ ረታ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ እንዳሉት በሀገር ግንባታ ኢደት ውስጥ መንግስት ብቻውን የሚሰራው ስራ እንደሌለ በመገንዘብ እንደ ሀገር አንድ የሚያደርጉን ጉዳዮች ላይ በመግባባት የግል ሴክተሮች ሚዲያዎች ከሌላው ከማህበረሰቡ ጋራ በጋራ በመስራት ኢደት ውስጥ የመጣውን የለውጥ ጉዞ በህዳሴ ግድብ መታየቱ የሚታወስ መሆኑን በመጥቀስ

እንደ ሀገር በማንኛውም ጉዳይ ላይ ድምፅ በመሆን ሰፊውን ማህበረሰብ በመወከል አብሮ በመስራት ላይ ስለምንገኝ በከተማ ደረጃ ትላልቅ ስራዎችን በመስራት አመርቂ ውጤት የታየበትና የማንሰራራት ህሳቤ ጉልቶ የሚታይበት ስራ እየሰራን እንገኛለን በማለት የለውጡ አንዱ ማሳየ የሆኑት በቢሮው ደረጃ የተፈቱና እየተፈቱ የሚገኙ ቅሬታዎችና መልካም አስተዳደሮች መሆናቸውን ጭምር አብራርተዋል ።

አቶ ገብሬ ዳኘው የቢሮው አማካሪ በበኩላቸው ቢሮው ባለፍት ሩብ አመት ውስጥ በብዙ ውጣ ውረድ ውስጥ ያለፈበት የአደባባይ በዓላት ያለ ምንም የጸጥታ ችግሮች ከመከበሩ አንስቶ በዚህ ውስጥ ከመሆን በተጨማሪ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን እየፈታ እንደሚገኝ ጠቁመው ህብረተሰቡን በማሳተፍ ችግሮችን ቀድሞ ለይቶ በመሰብሰብ የተሰራ ስራ መሆኑንና የተሰራው ስራና የመጣው ለውጥም የዚህ ውጤት በመሆኑ ይኔንን በቀጣይም አጠናክሮ ማስኬድ ይገባል ሲሉ ሀሳባቸውን ገልጸዋል።

በመጨረሻም አቶ ብርሀኑ ረታ የቢሮው ም/ቢሮ ሀላፊ መድረኩን በመሩበት ወቅት ከህብረተሰቡ ጋር ተግባብቶ በመስራትና ቢሮው በተሰጠው ስልጣንና ሀላፊነት መሰረት እኩል አገልግሎት እየሰጠና በተገቢው መንገድ እየሰራም እንደሆነና ቢሮውን በተመለከተ ጉዳይ ሁሉ ያሉ ክፍተቶች እንደሚፈቱና የተረጋጋ የፖለቲካ የኢኮኖሚ ስርአት በመዘርጋት ህብረተሰቡን ይዘን የማንሻገረውና የማንወጣው ችግር ስለማይኖር በጋራ በመሆን ሀገር በብዝሀነት የደመቀች ከተማ በመሆኗ ከተማውን የሚመጥን አግልግሎት በመስጠትና ሰላምና ጸጥታን በማረጋገጥ ሃላፊነታችንን እንወጣለንም ሲሉ ተደምጠዋል።

በአንደኛ ሩብ አመት ውስጥ በመልካም አስተዳደርና ቅሬታና አቤቱታ አፈታት ላይ የተሰሩ ስራዎችን ሪፖርት ያቀረቡት ወ/ሮ አለምጸሀይ ማሞ የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ስታንዳርዳይዜሽን አገልግሎት ዝግጅት ክትትልና ምዘና ዳይሬክቶሬ ዳይሬክተር ሲሆኑ በቀረበው ሪፖርት ላይ ከተሳታፊዎች ለቀረበው ሀሳብና አስተያየት ሀላፊዎቹ ምላሽ በመስጠት ውይይቱ ተጠናቋል።

በውይይቱ ላይ አቶ ብርሀኑ ረታ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ፣አቶ ገብሬ ዳኘው የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ አማካሪን ጨምሮ ባለድርሻ አካላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።