የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የፍትህና መልካም...

image description
image description
image description
image description
- recent news   

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የፍትህና መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ የቢሮውን የ1ኛ ሩብ አመት ዕቅድ አፈፃፀም ገመገመ።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የፍትህና መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ የቢሮውን የ1ኛ ሩብ አመት ዕቅድ አፈፃፀም ገመገመ።

ጥቅምት 7/2018 ዓ/ም (አዲስ አበባ)

**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላም የፍትህ መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴዎች የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላምና ጸጥታን የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት የተሰሩ የዕቅድ ሪፖርት አፈፃፀም ስራዎችን የቢሮው ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ገምግመዋል፡፡

በግምገማው መድረክ ላይ የቢሮውን ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በዝርዝር ያቀረቡት ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ ሲሆኑ ካቀረቡት ሪፖርት ውስጥ ዋና ዋናዎቹ

ቀደም ተብሎ በ2018 ዓ.ም ዕቅድ ላይ ላይ ህብረተሰቡን በማወያየትና ወደ ትግበራ በመግባት የተለያዩ አደረጃጀቶችን በመፍጠር ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት የማድረግ፣የከተማውን ሰላምና ጸጥታ ማረጋገጥ፣በቢሮው አገልግሎት ፈልገው ወደ ተቋሙ ለሚመጡ ልዩ ፍላጎት የሚያስፈልጋቸውን ግለሰቦች ምቹ ሁኔታ የማመቻቸት፣ቴክኖሎጂዎችን በቢሮው ውስጥ በማዘመን ቀልጣፍና ፈጣን አገልግሎት እንዲሰጡ መደረጋቸው፣የመልካም አስተዳደር ችግሮችን የመፍታት፣የሰራተኛው አቅም በየግዜው የማጎልበት፣ከተቋማት ጋር በቅንጅታዊ አሰራርና አተገባበር ማሳደግ፣ከሸገር ከተማ አስተዳደር ጋር አብሮ የመስራት፣የአቅመ ደካማ ቤቶችን የማደስ፣የሰላም ኮንፈረንሶችን በማዘጋጀትና ህብረተሰቡን በየግዜው በማወያየት የአደባባይ ክብረ በዓላት በሙሉ ፍጹም ሰላማዊ ሆነው እንዲከበሩ የማድረግ፣አዲስ የሰላም ስራዊት አባላትንና የቅጥር ጥበቃዎችን

በመመልመል በማሰልጠን በማስመረቅ ወደ ስራ እንዲገቡ የማድረግ፣የኑሮ ግሽበትን የመቆጣጠር የመከላከል፣የማህበረሰብ ተኮር ውይይቶች፣የጸጥታና መረጃ ስርአትን አጠናክሮ በማሽኬድ የህብረተሰቡን የጸጥታ ስጋት የመቀነስ ስራ መሰራቱን በሪፖርት በመግለጽ በቀጣይም የሚሰሩ ስራዎችንም ሀላፊዋ በሚገባ አብራርተዋል ።

ዶክተር ወርቅነሽ ምትኩ የፍትህና መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ጸሀፊ በበኩላቸው የጸጥታ ስራ እጅግ አድካሚ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆንም በብዙ ውጣ ውረድ ውስጥ በመሆን ከተማዋ በየግዜው የምታስተናግደውን ትላልቅ ሁነቶች በሰላም እንዲከበሩ ከማድረግ ባለፈ ከተማዋ ሰላሟ የተረጋገጠባት ለኑሮ ምቹ ነዋሪው በሰላም ወቶ የሚገባበት እንዲሆን ከማስቻል አንጻር ቢሮው እየተወጣ ያለውን ከፍተኛ ሀላፊነትና አስተዋፅኦ በመወጣቱ አመስግነዋል።

የቋሚ ኮሚቴዎቹ አባላት በሪፖርቱ ላይ ለተነሱት ሀሳብና አስተያየት በሰጡበት ወቅት እንደተናገሩት ቢሮው ከግዜ ወደ ግዜ አቅሙን እያጎለበት በመምጣቱ በተከታታይም አመታት በከተማው አስተዳደር ተሸላሚ እንዲሆን ያደረገውም ጠንክሮ በመሰራቱ መሆኑን በመጠቆም በይበልጥም የለማውን ቴክኖሎጂ ህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎች ቁጥጥር ላይና ሌሎችም ስራዎች ላይ የሚሰሩትን ስራዎች አበረታተው በቀጣይ ቢሮው አጠንክሮ ሊሰራው ስለሚገባው ጉዳይ ላይ ሀሳባቸውን ገልጸዋል።

በመጨረሻም ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ ከቋሚ ኮሚቴዎቹ ለተነሱት ሀሳብና አስተያየት ምላሽ በሰጡበት ወቅት እንደተናገሩት ቢሮው እየሰራ ያለውን የሪፊርም ስራ በቀጣይ ቢሮው የተሰጠውን ስልጣንና ሀላፊነት በማወቅ የቢሮውን የስራ ባህርይ በመረዳት ለስራው ብቁ የሆነ ባለሙያን የማፍራት ስራ እየሰራ እንደሆነ ጠቁመው በየቦታውና በየግዜው አልፎ አልፎ የሚስተዋሉ አግባብነት የሌላቸው የወንጀል ድርጊቶችን በተቻለ መጠን ሁሉ እየተሰራናለጸጥታ ስጋት እንቅፋት የሚሆኑ ድርጊቶችን እየተለዩ እርምጃ እየተወሰደባቸው እንደሆነና ቢሮው ህግን የማስከበር ስራውን በቀጣይም አጠናክሮ እንደሚቀጥል ሀላፊዋ ገልፀዋል።