የቀጠለ ዜና
የከተማዋን ነባራዊ ሁኔታ የተረዳና የፀጥታውን አዝማሚያ በማወቅ ለስራ የሚተጋ፤ ከተማውን የሚመጥን አመራር እና ፈጻሚ ለመፍጠር የአቅም ግንባታ ስራ በቀጣይ ጊዜያት በስፋት እንደሚሰራ ተገለፀ፡፡
ጥቅምት 6/2018 ዓ.ም (አዲስ አበባ)
****
ቢሮው ከደንብ ማስከበር ባለስልጣን ጋር በመሆን የ2018 ዓ.ም የአንደኛ ሩብ አመት የስራ አፈጻጸም ግምገማ የሁለቱም ተቋማት አመራሮችና ዳይሬክቶሬቶች እንዲሁም የክ/ከተማና የወረዳ ፅ/ቤት ኃላፊዎች በተገኙበት በዛሬው ዕለት አካሂዷል።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የከተማዋን ነባራዊ ሁኔታ የተረዳና የፀጥታውን አዝማሚያ በማወቅ ለስራ የሚተጋ፤ ከተማውን የሚመጥን አመራር እና ፈጻሚ ለመፍጠር የአቅም ግንባታ ስራ በቀጣይ ጊዜያት በስፋት እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡
ኃላፊዋ አያይዘውም ተቋሙ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ በማስደገፍ በመስራት የአገልግሎት አሰጣጡን በማዘመን ምቹ የስራ ሁኔታን በመፍጠር የአግልግሎት አሰጣጥ ስርዓቱን መቀላጠፍና ከሌብነትና ከብልሹ አሰራር የፀዳ ማድረግ፣ የቅንጅታዊ ስራዎችን ማጠናከር እና አጋዥ የፀጥታ ሃይሎችን መመልመል፣ መደራጀት፣ ማጠናከርና ስምሪት በመስጠት ነዋሪውን የሰላሙ ባለቤት ማድረግ ላይ በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ተደርጎ እንደሚሰራባቸው ኃላፊዋ ገልፀዋል።
የደንብ ማስበር ባለስልጣን ዋና ስራአስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በበኩላቸው፤ በ2018ዓ.ም ሁለቱም ተቋማት በተረጋጋና በጥሩ ሞራል ከተለመደ አሰራር ውጭ እቅድ በማቀድና ስራዎችም ላይ በመናበብና በመቀናጀት በመስራት የ1ኛ ሩብ አመቱ አፈፃፀሙም የተሻለ መሆኑን ጠቅሰው፤ ለቀጣይም ቢሆን የህዝባችንን ስጋትና ጥያቄ በመስማት ያልተፈቱ ጉዳዮችን የአገልግሎች አሰጣጣችንን በማዘመን ተደራሽ መሆን እንደሚገባና አሁንም አልፎ አልፎ የሚስተዋሉ የሌብነትና የብልሹ አሰራር ስራዎችና የመልካም አስተዳደር ችግሮች በቀጣይ ጊዜያት በርብርብ መፍታት እንደሚገባ ገልጸዋል።
በመድረኩ ላይ የሁለቱም ተቋማት የዕቅድና በጀት ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳሬክቶሬቶች የ2018 ዓ.ም የአንደኛ ሩብ ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት በማቅረብ፤ በዚህ ሩብ አመት በዋናነት ከተሰሩት ስራዎች ውስጥ፦ የማህበረሰብ ተኮር ውይይቶች ማሳደግ፣ የማህበረሰብና የፀጥታ ስራዎችና የአደረጃጀት ምልመላ፣ ተቋማዊ የእቅድ ስርዓቶች በመዘርጋት የሰራተኛ የመፈጸም አቅም ማጎልበት፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮች መፍታት፣ የህዝብ ጥቆማዎች መደራጀትና መተንተን፣ ወንጀል መከላከል፣ የፀጥታ ኦፕሬሽን ስራዎች የግጭት አፈታትና፣ ከኢኮኖሚ አሻጥር ጋር ተያይዞ ከሌሎች ሴክተሮች ጋር በመቀናጀት ክትትል ማድረግና እርምጃ መውሰድ፣ የደምብ መተላለፍን መከታተል፣ መቆጣጠርና እርምጃ መውሰድ እንዲሁም ጠንካራ የፀጥታ መዋቀር በመሰማራትና ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት አህጉር አቀፍ፣ አገር አቀፍና ከተማአቀፍ ሁነቶችና ኮንፍረንሶች ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ የአደባባይ በዓላት በሰላም ተከብረው ማለፍ መቻሉን ገልጸዋል።
በመጨረሻም በስራ አፈጻጸም ግምገማው ላይ የተሳተፉ አመራሮችና ዳይሬክተሬቶች በቀረበው ሪፖርት ላይ አስተያየትና ጥያቄዎች አቅርበው ሰፊ የሆነ ውይይት ተደርጎበት በአወያዮች ምላሽ ተሰጥቶባቸው የቀጣይ የስራ አቅጣጫ በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል።
የግምገማ መድረኩ ላይም የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀትታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፣ የደንብ ማስበር ባለስልጣን ዋና ስራአስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራን ጨምሮ የሁለቱም ተቋማት ም/ቢሮ ኃላፊዎችና ስራአስኪያጆች፣አማካሪዎችና፤ ፅ/ቤት ኃላፊዎች እንዲሁም ዳይሬክተሬቶች ስራ አስተባባሪዎች ተገኝተዋል።