የቢሮው የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ የ2018 ዓ.ም አንደኛ ሩብ አመት መሪ ዕቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት አካሄደ።
የቢሮው የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ የ2018 ዓ.ም አንደኛ ሩብ አመት መሪ ዕቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት አካሄደ።
ጥቅምት 4/2018 ዓ.ም (አዲስ አበባ )
**
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ የ2018 ዓ.ም አንደኛ ሩብ አመት መሪ ዕቅድ አፈጻጸምን ከማዕከል እስከ ወረዳ ከሚገኙ የዘርፉ ባለሙያዎች ጋር ውይይት አካሂዷል።
በውይይቱ ላይ በመገኘት ሀሳባቸውን የገለጹት አቶ ሚደክሳ ከበደ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ እንዳሉት ቀን ከሌት በመስራትና ህዝቡን በማሳተፋ የሰላም ባለቤት ከማድረግም በተጨማሪ የነዋሪውን አቅም በማጎልበት አካባቢውን እንዲጠብቅ አደረጃጀት በመፍጠር የምንሰራው ስራ አሁንም ወደፊትም የሚሳካው የህብረተሰቡ አመለካከት ላይ በስፋት በመስራትና በማወያየት ግንዛቤም በመፍጠር እንደሆነም ሀላፊው አንስተዋል ።
ሀላፊው አያይዘውም በሩብ ዓመቱ በተሰሩ ስራዎች ስኬታማ ለመሆን የተቻለው ህብረተሰቡ ጋር በሚኖረው የሀገር ግንባታ ስራዎችን ቀድሞ በመሰራታቸው በዓላት ያለ ምንም የጸጥታ ችግር የተከበሩበት ሀገር እንደ ሀገር ከፍ ብላ የታየችበት የአደባባይ በዓላቶች ወንድማማችነት አንድነት ጎልቶ ለአለም የታየበት የሽብር ሀይል ሴራ የከሸፈበት ሆኖ በስኬት የታለፈበት ሆኖ እንዳለፈው ሁሉ በቀጣይም የተጀመረውን ስኬት አጠናክሮ ማስኬድ እንደሚገባ አቶ ሚደክሳ ከበደ ተናግረዋል ።
የዕቅድ ሪፖርቱን ያቀረቡት አቶ ልቅናው ታሪኩ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ቡድን መሪ ሲሆኑ በ2018 ዓ.ም ታቅደው ወደ ትግበራ በመግባት በሩብ አመቱ የተከናወኑትን ተግባራት በተመለከተ በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት ከማድረግ ጀምሮ ነባር የቅጥር ጥበቃና አዲስ የሰላም ሰራዊት አባላትን መልምሎ አሰልጥኖ ወደ ስራ የማሰማራት፣ከተሰሩት ዋና ዋና ተግባራት ውስጥ መሆናቸውን ከቀረበው ሪፖርት ለመረዳት ተችሏል ።
በቀረበው ዕቅድ ሪፖርት ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጎ ለተነሳው ሀሳብና አስተያየት ምላሽ ተሰጥቷል ።
በውይይቱ ላይ አቶ ሚደክሳ ከበደ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ፣ከማዕከል እስከ ወረዳ የሚገኙ የዘርፉ ባለሙያዎች፣አስተባባሪዎችና ቡድን መሪዎች ተሳትፈዋል።