የአዲስ_አበባ_የሃይማኖት_ተቋማት_ጉባኤ_13ኛ_መ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የአዲስ_አበባ_የሃይማኖት_ተቋማት_ጉባኤ_13ኛ_መደበኛ_ጠቅላላ_ጉባኤ_በአደዋ_ሙዚየም_ተካሄደ።

#የአዲስ_አበባ_የሃይማኖት_ተቋማት_ጉባኤ_13ኛ_መደበኛ_ጠቅላላ_ጉባኤ_በአደዋ_ሙዚየም_ተካሄደ

****

መስከረም 29 ቀን 2018 ዓ.ም (አዲስ አበባ)

የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ 13ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤዉን በማካሄድ፤የ2017 ዓ.ም የስራ አፈጻጸም ሰላምን ከማጎልበት አንጻር የተገኙ ዉጤቶችንና የታዩ ዉስንነቶችን በመገምገም፤በ2018 ዓ.ም እቅድ ላይ ምክክር በማድረግ ለሰላም ግንባታ ሂደቶች የጋራ ተግባቦት በፍጠር ጉባኤዉ የተሳካ እንዲሆን ከአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጋር ሲሰሩ ለነበሩ የሃይማኖት ተቋማት፣ የመንግስት ተቋማትና የሚዲያ ተቋማት እዉቅና ሰጥቷል።

በጉባኤው ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ዋና ጸሃፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ እንደገለጹት ፤ጉባኤዉ ከምስረታ ጀምሮ በሀይማኖት ተቋማት መካከል ሰላማዊ መስተጋብር እንዲጎለብት ዘርፈ ብዙ ስራዎች ሲሰራ መቆየቱን አዉስተዉ፤እንደ ማሳያም የኢትዮጵያ አርቶዶክስ ተዋህዶ የሲኖዲዮስ ጉባኤ አባቶችን መርጦ ያሳለፈበት፣የህዝበ ሙስሊሙ ሰላማዊ የመጅሊስ ምርጫ እንዲካሄድ የተደረገበትና ሀይማኖታዊ የአደባባይ በዓላት በሰላም ተከብረው እንዳያልፍ አስተዋጽኦ እንደተበረከ ጠቅሰዋል።

መጋቢ ታምራት አክለዉም እንደ ሀገርም እንደ ከተማም ለተገኘዉ ድልና ለተገኙ ስኬቶች ሁሉ የመሪነት ሚናቸዉን ለተወጡ በየደረጃዉ ያሉ የመንግስት አመራሮችን በማመስገን፤በሃይማኖቶች መካከል የቆየዉን የአብሮነት እሴቶችን ሊያደበዝዙ የሚሞክሩ ከግጭት አትራፊ የሆኑ የየትኛውንም የእምነት ተቋም የማይወክሉ አካላትን ጉባኤዉ የማይታገስ ስለመሆኑ አንስተዉ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም አሳስበዋል።

የእለቱ የክብር እንግዳ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ ለ13ኛ ጠቅላላ ጉባኤው የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዉ፤ሀገራችን ኢትዮጵያ ብዙ ሀይማኖቶች ተከባብረው የሚኖሩባት እና የሀይማኖት ቋማት የሰላም ምንጭና ባለቤት እንደሆኑ ያነሱ ሲሆን፤የጋራ የሆኑ የሰላም የልማት ስራዎች፣በከተማዋ የተካሄዱ የአደባባይ ሁነቶች ያለምንም ኮሽታ እንዲከበሩ መደረጉና ሀይማኖታዊ ምርጫ በሰላም መጠናቀቁ የሀይማኖት ተቋማቱ ለሰላም ያላቸዉን ቀናኢነትን የሚያመለክት ነዉ ሲሉ ገልጸዋል። ሃላፊዋ በቀጣይ በከተማችን የሚከበሩ ሀይማኖታዊ ትልልቅ በዓላት፣የ2018 ዓ.ም ሀገር አቀፍ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቁ በሀይማኖት ተቋማት ስም ሌላ እኩይ ተግባራት እንዳይፈጸም ሲሉም ተደምጠዋል።

በጉባኤዉ ላይ ብጹዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባ፤ የየሀዲያና የስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዬ የቦርድ ሰብሳቢ፤ የኢትዮጲያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባዬ ጠቅላይ ፀኃፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ እና ሼህ ሱልጣን አማን ኤባ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክርቤት ሰብሳቢም እንዲሁ በጉባኤው ላይ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ 13ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤዉ ላይ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸኃፊ፤ የአዲስ አበባ እና የኦሮሚያ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤዎች ዋና ጸኃፊዎች፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፣የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋውን ጨምሮ ሌሎች የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ጉባኤዉ ተካሂዶ የእውቅና እና ሽልማት መርሃግብር ተካሂዷል።

በመጨረሻም በቀረበው የ2017 አፈጻጸም ሪፓርትና የ2018 ዓ.ም እቅድ ዙሪያ ከጉባኤው ተሳታፊዎች ሰፋ ያሉ ሀሳብና አስተያየቶች በማንሳት ሰፊ ውይይት ተደርጎ መድረኩ ተጠቃሏል።