በመልካም አስተዳደር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።
በመልካም አስተዳደር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።
**
መስከረም 27/2018 (አዲስ አበባ)
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ከ11ዱም ክፍለ ከተሞች ለተወጣጡ የተለያዩ አደረጃጀቶችና ለህብረተሰብ ክፍሎች በመልካም አስተዳደር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።
መድረኩ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ አማካሪ አቶ ገብሬ ዳኘው ንግግር ባደረጉበት ወቅት ለአገራችን እድገት መልካም አስተዳደር ትልቅ ሚና እንዳለው ጠቅሰው የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ እና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን በርትተን መስራት ይገባል ብለዋል፤ ይህ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር መካሄድ የተፈለገበት ምክንያት የመልካም አስተዳደር ችግሮች ከተለያየ የስራ መስክ ላይ የሚከሰት በመሆኑ ነው በማለት የስልጠናው አላማ በመልካም አስተዳደር ችግሮች ለይተን በመረዳት እንድንታገል ለማድረግ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የለውጥና የመልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ አለምጸሃይ ማሞ በበኩላቸው የመልካም አስተሳሰብ ችግሮች እንዲሁ በቀላሉ የሚፈቱ ሳይሆን ተጠያቂነት የሚጠይቅ ስራ በመሆኑ መጀመሪያ እራሳችንን ከብልሹ አሰራር አስተሳሰብ በመረዳት ሌላው የመልካም አስተዳደር ችግሮች መታገል ያስፈልጋልና ምቹ ያልሆኑ ብዙ ሁኔታዎች ቢኖሩም ተስፋ ባለመቁረጥ መታገል ይኖርብናል ብለዋል።
የስልጠና ሰነዱን ያቀረቡት የከንቲባ ጽ/ቤት የመልካም አስተዳደርና አቤቱታ የስልጠና ባለሙያ አቶ አስማማው ሙሉጌታ ሲሆኑ፤ መንግስታዊ አስተዳደር መልካም ወይም መልካም እንዳይሆን የሚያደርጉ ጉዳዮች የአስተዳደር ስርአትን በማስፈን ረገድ ሚና ያላቸው ህግ አውጪ፣ ህግ ተርጓሚ እና ህግ አስፈጻሚ ለመንግስታዊ አስተዳደር ያላቸውን ሚና ገልፀው፤ የመልካም አስተዳዳር እንቅፋት እየሆነ ያለው ትልቁ ችግር ሙስናና ኪራይ ሰብሳብነት፣ የፖለቲካ አመለካከት፣ የግልጽነት ጉድለት እና የመልካም አስተዳደር መሪዎች ተግባራዊ አለመሆናቸው ነው ብለዋል።
በመጨረሻም በቀረበው ስልጠና ሰነድ ላይ ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ መድረኩ ተጠናቋል።