ቢሮው በ2018 ዓ.ም በ1ኛዉ ሩብ ዓመት በታቀደው ዕቅድ ላይ የተከናወኑ ተግባሮች ድጋፍና ክትትል ለሚያደርጉ የቡድን አባላት ግንዛቤ ሰጠ።
ቢሮው በ2018 ዓ.ም በ1ኛዉ ሩብ ዓመት በታቀደው ዕቅድ ላይ የተከናወኑ ተግባሮች ድጋፍና ክትትል ለሚያደርጉ የቡድን አባላት ግንዛቤ ሰጠ።
*****
መስከረም 20/2018ዓ.ም(አዲስአበባ)
ይህ ድጋፍና ክትትል ያስፈለገበት ዋና ዓላማ ከፊታችን የሚካሄደው የሃይማኖት ተቋማት ጠቅላላ ጉባኤ መነሻ እንዲሆንና ምክክርሩ ህግና ህገ መንግሥቱን መሠረት ያደረገ እንዲሁም በመንግሥት እና በሀይማኖት መካካል
እንደ መንግሥት ከመንግሥት የሚጠበቁ ጉዳዮችን፣የመስክ ምልከታ የድጋፍና ክትትል ለማድረግ እንደሆነ፤ የአዲስ አበባ ከተማ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የኃይማኖት ጉዳዮችና የሰላም ዕሴት ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ረታ ገልጸዋል።
ሀላፊው አክለውም የሀይማኖት ተቋማት የሚወክላቸው የመንግሥትን ድጋፍ የሚሹ ጉዳዮች፣የዝግጅት ምእራፍ ስራ ስምሪት የምናደርግበት ነው በማለት ከወረዳ እስከ ማዕከል የሚፈቱ ችግሮችን ለይቶ ስራዎችን መስራትና ህዝቡን የሰላም ባለቤት ከማድረግ ጋር ተያይዞ በቀጣይ ለሁለተኛ ሩብ ዓመት በጠንካራ ጎን የታዩትንበመውሰድ በደካማ ጎን የታዩትን ደግሞ በመቅረፍ የሚሰማራው ቡድን ስምሪት የሚወጣበትና በዘርፋችን ልንሰራቸዉ የሚገቡ ተግባሮችን በመስራት ሰላሟ የሰፈነባት ከተማ ለማድረግ የታለመ ስምሪት ነው ብለዋል።