የመከላከለያ ሰራዊት በእጩ መኮንን ደረጃ ለስልጠና የሽኝት መርሃግብር
"መከላከያ ሙሉ ሰዉ የሚያደርግ ተቋም ነዉ"
#አቶ_ተስፋዬ_ደንድር_ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትል የቢሮ ሀላፊ
**
መስከረም 20/2018 ዓ.ም(አዲስአበባ)
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ በከተማዉ ዘላቂና አስተማማኝ ሰላምን ለማረጋገጥ እና የመከላከለያ ሰራዊትን በሰው ሀይል ለማጠናከር በዕውቀትና በቴክኖሎጂ ለመደገፍ ያስችል ዘንድ በ11ዱም ክፍለ ከተማ ሲደረግ የነበረዉ የሰዉ ሀይል ምልመላ በእጩ መኮንን ደረጃ ለስልጠና የሽኝት መርሃግብር ተካሄደ።
በሽኝት መርሃግብሩ አቶ ተስፋዬ ደንድር የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትል የቢሮ ሀላፊ ባስተላለፉት መልእክት እንደገለፁት፤ከናንተ አልፋችሁ ሀገራችሁን እና ወገኖቻችሁን የምታገለግሉበት ስለሆነ ትልቅ እድል ነዉ በማለት፤ሀገርን በፈቃደኝነት ማገልገል በአካልና በአእምሮ ብቁ የሆነ የተማረ ሀይል በእጩ መኮነንን ደረጃ በመመልመል ይሄን እድል ስላገኛችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
አቶ ተስፋዬ አክለዉም የመከላከያ አባልነትን ለመቀላቀል ብዙ መስፈርት መታለፍ እንደሚገባ አዉስተዉ፤ መከላከያ በስነምግባር እና በአካል በማብቃት ሙሉ ሰዉ የሚያደርግ ነዉ በማለት ፤የከተማውን ስም የምታስጠሩ ጀግኖች እንድትሆኑ በማለት አሳስበዋል።
ኮረኔል አስናቀ ተሰማ በበኩላቸው በሀገራችን ዉትድርና ዘምኖ አለም እየተጠቀመበት ያለዉን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ከሳይንስ ጋር የተላመደ ሀይል አስገብተን በእጩ መኮንንነት ለመጀመሪያ ጊዜ በመመልመላችሁ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት መከላከያ ለአነጋገሩ ለአመጋገቡ ሁሉ ህግ ያለዉ በመሆኑ መማር መሠልጠን የሚፈልግ ስለሆነ ወደ ወጣትነት ወኔያችሁ እንድትመለሱ ብለዉ ከ አደራ ጭምር አሳስበዋል።
በሽኝቱ ላይ አቶ ተስፋዬ ደንድር የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትል የቢሮ ሀላፊ፣የ11ዱም ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ሀላፊዎች፣የወረዳ ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ሀላፊዎችን ጨምሮ የሚመለከታቸው የመከላከያ አባላትና ሽኝቱ የተደረገላቸው እጩ ምልምሎች ተገኝተወዋለል፡፡