በቀጣይ ሳምንታት የሚከበሩ የመስቀል እና ኢሬቻ በዓላት በሰላም ተከብረው እንዲያልፉ ሴቶች ትልቅ ሚና እንዳላቸው ተገለጸ። *
በቀጣይ ሳምንታት የሚከበሩ የመስቀል እና ኢሬቻ በዓላት በሰላም ተከብረው እንዲያልፉ ሴቶች ትልቅ ሚና እንዳላቸው ተገለጸ።
*
መስከረም 12/2018 (አዲስ. አበባ)
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ በቀጣይ ሳምንታት የሚከበሩ የመስቀል እና ኢሬቻ በዓላት ያለምንም የጸጥታ ችግር ተከብረው እንዲያልፉ ለማድረግ ከብሎክ ጀምሮ ሲያወያያቸው የነበረውን አካላት በከተማ ደረጃ ከአዲስ አበባ ከተማ ሴት ማህበር ጋር የማጠቃለያ የውይይት መድረክ አካሂዷል።
በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፤ ሀገራችን ዘርፈ ብዙ ጉዳዮችን አሳክታ በማንሰራራትና በእምርታ የምናከብረው የ2018 ዓ.ም የመስቀል እና የኢሬቻ በዓላት ዋዜማ ሳምንት አደረሳችሁ ብለው፤
ሴቶች የተሰጣቸውን የትኛውም ሃላፊነት መውጣት እንደሚችሉ መሆኑን የሚያሳይ ከግማሽ በላይ የሚሆኑ የሰላም ሰራዊት አደረጃጃት ውስጥ በመሳተፍ አካባቢያቸውን እየጠበቃችሁ እንዲሁም የሴቶች ማህበር የተለያዩ የሰላምና ፀጥታ ዙሪያ በርካታ ስራ መስራታቸውን ጠቅሰዋል።
ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ አክለውም ሴቶች የተሰጣቸውን የትኛውም ሃላፊነት በመወጣት አከባቢያቸውን በመቃኘት ሃይማኖትን ሽፋን አድረገው ችግር መፍጠር የሚፈልጉ ፀጉረ ለውጥ አካላትን ጥቆማ በመስጠት እንዲሁም በጨዋ ኢትዮጵያዊ እሴታችን እንግዳ በመቀበል ባህላችን በቀጣይ ሳምንት የሚከበሩ የመስቀል እና ኢሬቻ በዓላት በሰላም ተከብሮ እንዲያልፉ ሚናቸው መውጣት እንደሚገባ አሳስበዋል።
መድረኩን የመሩት አቶ ሚደክሳ ከበደ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/የቢሮ ሀላፊ በበኩላቸው
ኢትዮጵያውያን ሲተባበሩና አብረው ሲቆሙ ያላቸውን ሀይል ለአለም የተገለጸበት ዳግማዊ አድዋ ያስመሰገብነበት ወቅት በመሆኑ የ2018ዓ.ም በአላት በልዩ ደስታ እናከብራለን፤ ደስታችን የሚያስከፋቸውና የኢትዮጵያ ከፍታ የማይፈልጉ አካላት ባንዳ በመላክ የከተማችን ሰላም እንዳያደፈርስ መጠንቀቅ ይኖርብናል።
ስለዚህም ከፊታችን ያሉትን በአላት ባህላዊ እሴቶችና ሃይማኖታዊ ቱፊታቸውን ጠብቀው እንዲከበሩ ለማድረግ እኔ ለከተማዬ የሰላም ዘብ ነኝ በማለት የአየር ሁኔታ ሳይበግራችሁ ለሰላም ቅድሚያ የምትሰጡ ሴቶች ጉልህ ሚና አላቸው በማለት ደመራ የሚደመርበትን ቦታ ለይታችሁ በማስተባበር በዓሉን የፖለቲካ ማራመጃ ሜዳ ማድረግ የሚፈልጉ አካላትን መከላከል እንዳለባቸው ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ የሴት ማህበር ሰብሳቢ የሆኑት ወ/ሮ እናታለም እንዳለ በበኩላቸው እነዚህ የአደባባይ በዓላት በአለም አደባባይ ሃገራችንን ያስተዋወቁ በመሆናቸው ከአገር ውጭ ለጉብኝት የሚመጡ ቱሪስቶችን አንድነታችንና አብሮነታችን በማሳየትና በእንግዳ ተቀባይነት ስሜት ተቀብለን ማስተናገድ ላይ ሁሉም ሚናውን መውጣት አለበት ብለዋል።
ለዉይይቱ መነሻ የሚሆን ከመስቀል ደመራ ጋር የተያያዘ ሰነድ በአቶ ማስረሻ ሃብቴ አማካኝነት ቀርቦ ሰፋ ያለ ጥያቄና አስተያየቶች ከተሳታፊዎች ተሰንዝሯል።
ከተወያያዮች በተነሱት ጥያቄና አስተያየቶች ዙሪያ ከአወያዮች ምላሽ ተሰጥቶ፤ በቀጣይ ቀናት በትኩረት መሠራት ያሉባቸው ጉዳዮች በአቅጣጫ መልክ ከመድረኩ መሪዎች ተሠጥቶ መድረኩ ተጠናቋል።