የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ለ12 ተከታታይ ቀናት...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ለ12 ተከታታይ ቀናት በንድፈ ሐሳብና በወታደራዊ መስክ ስልጠና ሲያሰለጥናቸው የነበረውን ነባር የአከባቢ የህዝብ ቅጥር ጥበቃ አባላት በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመረቀ።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ለ12 ተከታታይ ቀናት በንድፈ ሐሳብና በወታደራዊ መስክ ስልጠና ሲያሰለጥናቸው የነበረውን ነባር የአከባቢ የህዝብ ቅጥር ጥበቃ አባላት በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመረቀ።

***

መስከረም 12/2018 ዓ.ም(አዲስአበባ)

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ለ12 ተከታታይ ቀናት በንድፈ ሐሳብና በወታደራዊ መስክ ስልጠና ሲያሰለጥናቸው የነበረውን ነባር የአከባቢ የህዝብ ቅጥር ጥበቃ አባላት በዳግማዊ ሚኒሊክ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቅጥር ጊቢ በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል።

በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ የእለቱ የክብር እንግዳ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሀላፊ፣የቢሮዉ ምክትል ቢሮ/ሀላፊዎች፣የ11ዱም ክፍለ ከተማ የሰላምና ጸጥታ ጽህፈት ቤት ሀላፊዎች፣የየ ወረዳዉ የሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ሀላፊዎች፣ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የነባር ቅጥር ጥበቃ ተመራቂዎች እና ስልጠናውን ሲያስተባብሩ የነበሩ በየ ደረጃዉ ያሉ የፖሊስ አባላት ተገኝተዋል።

በምርቃቱ ላይ የመክፈቻ ንግግርና የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ያስተላለፉት አቶ ሚደክሳ ከበደ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ ሲሆኑ፤የወንጀል ምጣኔን የመቀነስ አንዱ አካል የሆነዉ ይሀዉ ስልጠና ከ5,800 በላይ የህዝብ የቅጥር ጥበቃ አባላት የተሳተፉበት የመስክና የንድፈ ሀሳብ ስልጠና የተቋም ማሻሻያ አንዱ አካል ከመሆኑ ባሻገር የከተማችንን ህዝብ በሰላምና ፀጥታ ስራዎች ላይ የሚያደርጉት ንቁ ተሳትፎ ማሳያ እንደሆነ ገልጸዋል።

የእለቱ የክብር እንግዳ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በበኩላቸው፤የመስክና የንድፈ ሃሳብ ስልጠና ስትከታተሉ የቆያችሁ የፀጥታ አጋዥ ሃይል ለሆኑት የህዝብ ቅጥር ጥበቃ አባላት የምረቃ በአል እንኳን ደስ አላችሁ ብለው፤

አዲስ አበባ ከተማ በአለም አቀፍ ብሎም በአፍሪካ ደረጃ ያላትን የከተማነትና የፖለቲካ ማዕከልነት ደረጃ የሚመጥን ፀጥታ ለማስጠበቅና የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት ከተማ ለማድረግ የህግ የበላይነት ሊያስከብሩና ሊያረጋግጡ የሚችሉ በእውቀትና በአመለካከት የታነፀ የሰው ኃይል እና ግብአት የተሟላላቸው ዘመናዊ የህግ አስከባሪ ተቋማት ሊኖራት ይገባል ሲሉም ተደምጠዋል።

ሀላፊዋ አክለዉም የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በከተማው ውስጥ የሚስተዋሉትን የህግ ጥሰቶች ወንጀሎች እና የፀጥታ ችግሮች በመከላከልና በመቆጣጠር የአካባቢውን ፀጥታና የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በብቃት ላይ የተመሠረተ ተቋማዊ አደረጃጀት መፍጠር ያስችለው ዘንድ ሰፊውን የከተማውን ህዝብ በማስተባበር ተቀጥረው በስራ ላይ የሚገኙትን የህዝብ ቅጥር ጥበቃ አባላት ከፀጥታ ተቋማት ጋር በመተባበር በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ላለፉት ቀናት ሙያዊና የአመለካከት የአቅም ግንባታ ስልጠና እንዲወስዱ መደረጉን አዉስተዉ፤ተመራቂዎችም ከሌሎች የጸጥታ መዋቅሮች ላይ በቀናጀት የከተማውን ሰላም ለማስጠበቅ የሠለጠኑትን በተግባር እንዲያሳዩ አሳስበዋል።

በመጨረሻም ለ11ዱም ክፍለ ከተማ አሰልጣኝ ፓሊሶች እና ለቅጥር ጥበቃ አባላት ተወካዮች የዋንጫና ሰርተፊኬት በማበርከት ምርቃቱ ተጠናቋል።